You are currently viewing በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ሁለተኛ ዙር ማንነት ተኮር የእገታ ወንጀል አሳዛኝ ሂደት እንደነበረው ከዐይን እማኝ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ሁለተኛ ዙር ማንነት ተኮር የእገታ ወንጀል አሳዛኝ ሂደት እንደነበረው ከዐይን እማኝ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ሁለተኛ ዙር ማንነት ተኮር የእገታ ወንጀል አሳዛኝ ሂደት እንደነበረው ከዐይን እማኝ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች ላይ ስለተፈጸመው አሳዛኝ ማንነት ተኮር የእገታ ወንጀል ከዐይን እማኝ ያገኘው መረጃ የሚከተለው ነው:_ ህዳር 29 እና 30/2015 ወደ ግቢ ግቡ በሚል የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት የመጣን የአማራ ተማሪዎች ከኦሮሞ እና ከደቡብ ልጆች ጋር በመሆን መነሻችንን ከአዲስ አበባ አስኮ መናኽሪያ አድርገን ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ጉዞ ጀምረናል። ብዛታችን 60 የምንሆን ተማሪዎች ህዳር 29 እና 30/2015 ወደ ግቢ ግቡ በመባሉ ህዳር 29/2015 በኦዳ ባስ ተሳፍረን እየተጓዝን ነበር። ጉዟችን ቀጥለን ነቀምት ምሳ ከበላን በኋላ ጊምቢን አለፍ ብለን ጉሊሶ ህዳር 29/2015 በግምት ከቀኑ 10:30 ስንደርስ ታጣቂዎች መስመር ላይ የመኪናውን ሰው በሙሉ አስወርደው ወደ 60 ሰው ነው፣ 25 ደቂቃ ወደ ጫካ ገባ ብለው ወስደው ነው ከዛ አማርኛ እና ኦሮምኛ ተናጋሪን በማናገር ሰላምታ እና ሌላ ብዙ ነገር በማውራት በማናገር የማይችለውን ለብቻ፣ የሚችለውን ለብቻ በማድረግ ነው የለዩት። ከዛ በመቀጠል ኦሮምኛ ተናጋሪ በሙሉ መሄድ ትችላላችሁ ተባሉ፤ ሌላው አማርኛ ተናጋሪ ተለይቶ ቀረ። ቁምጣ የለበሱ ከ4 በላይ ታጣቂዎች በመኪና መንገዱ ዳር እና ዳር ሆነው ሾፌሩን ቁም በማለት ነበር ያስቆሙት። አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ 14 የሚሆኑ ተማሪዎችን ለይተው ካስቀሩ በኋላ ከደቡብ ክልል የመጡ ልጆችን ደግሞ መታወቂያ በማዬት እንዲሄዱ ፈቀዱላቸው። ከመካከላቸው ደጀን የሚባለው ልጅ እሱ ራሱ ከደቡብ ነው የመጣሁት ከሀዋሳ ነው ሲል እስኪ በቋንቋ አናግረኝ፣ በሲዳምኛ አናግረኝ ሲለው አላውቅም ሲለው፤ አይዲውን/መታወቂያውን ተቀበለ እና አዬ፤ አይዲውን ሲያይ ደጀን ያለው ይላል፤ አንተማ የአማራ ስም ነው የያዝክ የአማራ ልጅ ነህ ብሎ አስቀረው። በአጠቃላይ 9 የአማራ ልጆችን ለይተው በጫካ አስቀሯቸው። የተማሪዎችን ቦርሳ አውርደው በመጣል መኪናውን እንዳቃጠሉት አይተናል። ከመካከላቸው አንደኛው ከነቀምት የሄደ የኦሮሞ ልጅ “ኧረ ተማሪዎች ናቸው” በማለቱ “ማልቴ ማለቴ” በማለት ሄደው ሰፈሩበት እና አንተንም እንጨርስሃለን ሲሉት በኦሮምኛ አታለላቸው እና ሄደ። ጊዜው መሽቷል፤ 12:30 ስለነበር በጉሊሶ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጠግተን አደርን፤ የአካባቢው ሰዎችም አይዟችሁ ሁሌም ያለ ነው በማለት ተንከባክበው አሳደሩን። በጠዋቱ ደውለው ጣይራ ከሚባል አካባቢ መኪና በማስመጣት ህዳር 30/2015 ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ከቀኑ 9:30 አካባቢ ገባን። በመጨረሻም ከዘጠኙ ታጋች በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የአማራ ልጆች መካከል አንደኛዋ በህይወት ስለመትረፏ የነገሩን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጭ ህዳር 25/2012 በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ 17 የአማራ ልጆች በኦነጎች ታግተው እስካሁን ደብዛቸው ስለመጥፋቱ በመግለጽ ማዘናቸውን ተናግረዋል። እየተሰራበት ባለው በጭካኔ የታገዘ መዋቅራዊ እና ስርዓታዊ ሸፍጥ እና ሴራ፣ በሚፈጸምበት ሁለንተናዊ ጥቃት እረፍት የተነሳው አማራ ከሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቹ ጋር በመሆን በሰራት ሀገሩ ኢትዮጵያ ላይ ባይተዋር እና ባለቤት አልባ እንዲሆን እየተደረገ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ባለው በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ሲማሩ የነበሩ የአማራ ተማሪዎች በተለያዩ ጊዜያት የድንጋይ ዘመንን የሚያስንቁ፣ የጨካኞች መጫዎቻ እየሆኑ ነው። በነውረኛ ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ኦነጋዊያን ህዳር 25/2012 ዓ.ም እና ህዳር 29/2015 ታግተው ደብዛቸው እንዲጠፋ የተደረጉ 25 የአማራ ተማሪዎች ስም ዝርዝር:_ 1. በላይነሽ መኮንን ደምለዉ (የ1ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተማሪ)፣ 2. ሳምራዊት ቀሬ አስረስ (የ2ኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪ)፣ 3. ዘዉዴ ግርማዉ ፈጠነ (የ3ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተመራቂ ተማሪ)፣ 4. ሙሉ ዘዉዴ አዳነ (2ኛ ዓመት የማህበረሰብ ሳይንስ ጥናት ተማሪ)፣ 5. ግርማቸዉ የኔነህ አዱኛ (3ኛ ዓመት የባዮቴክኖሎጂ ተመራቂ ተማሪ)፣ 6. ስርጉት ጌቴ ጥበቡ (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ)፣ 7. ትግስት መሳይ መዝገቡ (የ12 ክፍል የመሰናዶ ተማሪ)፣ 8. መሰረት ከፍያለዉ ሞላ (የሶስተኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)፣ 9. ዘመድ ብርሃን ደሴ (የሶስተኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)፣ 10. ሞነምን በላይ አበበ (የ2ኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪ)፣ 11. ጤናለም ሙላቴ ከበደ (የ2ኛ ዓመት የእርሻ ምጣኔ ሀብት ተማሪ) 12. እስካለሁ ቸኮል ተገኝ (የኬሚስትሪ 3ኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪ)፣ 13. አሳቤ አየለ አለም (የ3ኛ ዓመት የእጽዋት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ) 14. ቢተዉልኝ አጥናፉ አለሙ (የ3ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራቂ ተማሪ)፣ 15. ግርማው ሀብቴ እመኘዉ (የ3ኛ ዓመት የመካኒካል ምህንድስና ተማሪ)፣ 16. አታለለኝ ጌትነት ደረሰ (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ)፣ 17. ክንድዬ ሞላ ገበየሁ (የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ) ናቸው። በተጨማሪም ህዳር 29/2015 በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ጉሊሶ ቀበሌ የታገቱ ተማሪዎች ስም ዝርዝር:_ 18) ቤዛ ተሾመ 5ኛ ዓመት የአርክቴክቸር ተማሪ፣ ከአዲስአበባ ፣ 19) ሰይዳ መሀመድ 5ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ፣ ከደባርቅ ፣ 20) ማህሌት ዘላለም 4ኛ ዓመት የማኔጅመንት ተማሪ፣ ከደብረ ማርቆስ ፣ 21) ሲሳይ ጋሻዬ 4ኛ ዓመት የሳይኮሎጂ ተማሪ፣ ከደብረ ማርቆስ ፣ 22) ደጀን ያለው 4ኛ አመት የአይቲ ተማሪ፣ ከደቡብ ጎንደር ፣ 23) ኪሩቤል መለሰ 5ኛ ዓመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ፣ ከጎንደር፣ 24) ቡዙአዬሁ አረጋ_የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ፣ የደብረ ብርሃን አካባቢ ልጅ፣ 25) ብርሀኑ አበባው የ5ኛ ዓመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ፣ ከባህርዳር መሆናቸው ታውቋል። ህዳር 29/2015 ከታገቱት 9 የአማራ ተማሪዎች መካከል አንደኛዋ አምልጣም ይሁን ሆንተብሎ ተለቃ አሁን ላይ በህይወት መኖሯ ታውቋል። 5 ሴቶች እና 3 ወንዶች በድምሩ 8 የአማራ ልጆች በጨካኝ ኦነጋዊያን ከታገቱበት ህዳር 29/2015 ጀምሮ ይህን መረጃ እስካጋራንበት ጊዜ ድረስ ስላሉበት ሁኔታ የተገኘ መረጃ የለም። በአጠቃላይ አማራ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ እንዲማሩ ከላካቸው መካከል 25 የሚሆኑ ልጆቹን በሁለት ዙር በተፈጸመ እገታ በጨካኝ ሰዋዊ አውሬዎች ተነጥቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply