በደረሰው አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፡፡ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ህንጻ ለመገን…

በደረሰው አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፡፡

ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏል ተብሏል፡፡

አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ በስራ ላይ እንዳሉ ስራዉ ከሚከናወንበት አጠገብ የነበረና አፋፍ ላይ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉሀ ልክና አፈር በሰራተኞቹ ላይ በመናዱ የደረሰ አደጋ ነው ሲል የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለጣበያችን ተናግሯል፡፡

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ከተጫነበት አፈርና ድንጋይ ስር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣበያችን እንደተናገሩት እየተገነባ ያለው ህንጻ እና የተደረመሰው ቤት የአንድ ግለሰብ መሆናቸው ነግረውናል፡፡

በማናቸዉም የግንባታ ስራዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ አለመስራት መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የግንባታ ፈቃድ ሰጪ አካላትም ተገቢዉን ክትትል ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply