በደራሼ ልዩ ወረዳ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከ200 በላይ ሰዎች ያሉበት አይታወቅም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ…

በደራሼ ልዩ ወረዳ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከ200 በላይ ሰዎች ያሉበት አይታወቅም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ ከባለፈው ሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከ200 በላይ ሰዎች የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ገልጸዋል። በአካባቢው ሚያዝያ 17/2014 በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በመንግሥትና በታጣቂ ኃይሎች መካከል በተደረጉ የተኩስ ልውውጦች የሞቱ፣ የቆሰሉና ሸሽተው ወደ ጫካ ገብተው ያልተመለሱ ሰዎች መኖራቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ከ10 በላይ ሰዎች እንደሞቱ እና ከ200 በላይ ሰዎች እንዲሁ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና የት እንዳሉ የማይታወቁ ሰዎች መሆናቸውንም ኃላፊው ጠቁመዋል። እስከ አሁን የት እንዳሉ አይታወቁም ከተባሉት ሰዎች መካከል የሞቱ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውና ጫካ ገብተው ያልተመለሱትን እንደሚጨምር ተመላክቷል፡፡ አዲስ ማለዳ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply