በደራ ወረዳ የእምቦጭ ማስወገድ ዘመቻው ተጀምሯል። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባህር ዳር /// በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳ ሀገራዊዉን እንቦጭ የማስወገድ እንቅስቃሴ…

በደራ ወረዳ የእምቦጭ ማስወገድ ዘመቻው ተጀምሯል። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባህር ዳር /// በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳ ሀገራዊዉን እንቦጭ የማስወገድ እንቅስቃሴ በወረዳዉ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ በዚሁ እንቦጭን የማስወገድ እንቅስቃሴ ሲሳተፉ ያገኘናቸዉ መርጌታ አባይ ፍስሀ እንደተናገሩት በዚህ ዓመት እንቦጭን የማስወገድ ሂደቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመቻ መካሄድ መቻሉ መልካም ጅማሮ ነዉ ብለዋል፡፡ላለፉት 8 ዓመታት በቀበሌም ሆነ በወረዳ ደረጃ ለማስወገድ ሲሞክር መቆየቱ ይታወቃል ሆኖም ግን ዉጤታማነቱ ከዚህ ግባ የሚባል አልነበረም ሲሉ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም መንግስት ትኩረት በመስጠት ጀልባና የማስወገጃ ማሽነሪዎችን እንዲሁም የሰዉ ጉልበት በመጠቀም በዚህ ደረጃ ለማስወገድ ርብርብ መካሄድ መቻሉ ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ ይረዳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሌላዉ አስተያየት ሰጭ አቶ አዲሱ መሰረት የእንቦጭ አረም ከተከሰተ በኋላ በተለይም በጣና አካባቢ ለሚኖረዉ ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ሲፈጥርብን መቆየቱ ያታወቃል ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ይህንን ችግር ግምት ዉስጥ በማስገባት ይህን አረም በዘላቂነት ለመስወገድ የጀመረዉ ዘመቻ ይበል የሚያስብል ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም እኛም ይህንን ሀገራዊ ጥሪ ግምት ዉስጥ በማስገባት ለማስወገድ መረባረብ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ መረጃው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply