በደሴ ከተማ 28 በመቶ ብቻ የሚሆኑት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ነጥብ እንዳመጡ የደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፤ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ቅሬታ እያሰሙ…

በደሴ ከተማ 28 በመቶ ብቻ የሚሆኑት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን ነጥብ እንዳመጡ የደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፤ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ቅሬታ እያሰሙ መሆናቸውም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የደሴ ከተማ አስ/ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅር አበበ በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 914 ሴት 858 በአጠቃላይ 1772 ተማሪዎች ፈተና ወስደው ወንድ 296 ሴት 298 በድምሩ 594 ተማሪዎች እንዳለፉ አስረድተዋል፡፡ በማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ደግሞ 363 ወንድና 694 ሴት ተማሪዎች ባጠቃላይ 1057 ፈተና ወስደው 51 ወንድና 115 ሴት በአጠቃላይም 166 ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸው ገልጸዋል፡፡ ያለፉትን ተማሪዎች ባጠቃላይ ወንድ 347 ሴት 417 ጠ/ድምር 760 ተማሪዎች ወይም 28.86 በመቶ ወደ ዩንቨርስቲ የመግቢያ ነጥብ ከተቆረጠው ውጤት በላይ ያመጡ መሆኑን ገልጸዋል። ከባለፈው አመት በ2012ዓም በማህበራዊ ሳይንስና በተፈጥሮ ሳይንስ ከተፈተኑት ውስጥ 60% ውጤት ሲያመጡ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በታች መሆኑን ገልጸዋል። ለውጤት ማነስና ዝቅተኛ መሆን ዋናው ምክንያት በደሴ ከተማና አካባቢው ከአራት ወር በላይ ጦርነት መካሄዱና የተማሪዎች የሥነ ልቦና ስብራት ሳይጠገንና ሳይረጋጉ በጦርነት ስነልቦና ጫና ውስጥ ሁነው መፈተናቸውና የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ከፍ ማለቱ ነው ብለዋል። ተማሪዎቹ የነበሩበትን ችግር ባላገናዘበ መልኩ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል የማለፊያ ነጥብ መደረጉ ፍትሃዊና አግባብ አይደለምም ብለዋል። በመግቢያ ውጤቱ አሰጣጥ ሁኔታም ተማሪዎችና ወላጆች ስሜት ውስጥ መግባታቸውንም ገልጸዋል፡፡ የማለፊያ ነጥቡ ከተማው የነበረበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያገናዘበ እንዲሆንም ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ማቅረባቸውንም አቶ ፍቅር አበበ ተናግረዋል፡፡ ደሴ ኮሚዩኒኬሽን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply