በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ መከሰቱ በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አንድ ሰው ሲሞት 31 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል ተባለ፡፡ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ በደቡብ ሱዳን የኮሌራ በሽታ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

በሽታው የተከሰተው በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ዩኒቲ ግዛት ሩቦንካ ካውንቲ ሲሆን በበሽታው ተጠቅተዋል የተባሉት ሰዎች ታክመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተሰምቷል፡፡ የደቡብ ሱዳን የጤና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የበሽታው ስርጭት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡

በሽታው መጀመሪያ በሁለት ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የተገኘ ሲሆን ፤አሁን ላይ በወረርሽኝ መልክ እንዳይሰራጭ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ደቡብ ሱዳን ከአምስት ዓመታት በፊት ባጋጠማት የኮሌራ ወረርሽኝ 436 ዜጎቿን በሞት መነጠቋን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስታውሷል፡፡በዓለማችን በየዓመቱ ቁጥራቸው ከ1 ነጥብ 3 እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮሌራ በሽታ እንደሚጠቁና ከነዚህ መካከል አነሰ ሲባል 21 ሺህ ሲበዛ ደግሞ 143 ሺህ ሞት እንደሚመዘገብ
የዓለም ጤና ድርጅትመረጃ ያሳያል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply