ርክክቡ ከመቀሌ ከተማ 36 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው “አጉላ ካምፕ” የተከናወነ ሲሆን በርክክቡ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ ታዛቢዎችም ተገኝተዋል።
በቀጠናው የተሠማራው የኢፌዴሪ ሠራዊት አመራር ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለ ÷ በመንግስትና በህዋሓት አመራሮች መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የተለያዩ ዓይነት ከባድ መሣሪያዎችን መረከባቸውን ገልፀዋል፡፡
ህወሓት ለመከላከያ ሠራዊታችን ያስረከባቸው የመሳሪያ ዓይነቶችም ብረት ለበስ ታንኮች ፣ የተለያዩ ሚሊ ሜትር መድፎች፣ ሮኬቶች፣ ዙዎች፣ ሞርተሮች እና ፐምፐን ያጠቃለለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post