በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የፀረ-መንግስት ተቃውሞ ከመደረጉ አስቀድሞ 87 ሰዎች መታሰራቸው ተገለፀ።

የደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ሃይሎች የግራ ክንፍ የኢኮኖሚ ነፃነት ተዋጊዎች ፓርቲ ሊያካሂደው ካቀደው የተቃውሞ ሰልፍ በፊት በመላ ሀገሪቱ ባለፉት 12 ሰዓታት ውስጥ 87 ሰዎችን ማስሩ ታውቋል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ ሶስተኛና ትልቁ ፓርቲ ኢ. ኤፍ. ኤፍ የኃይል መቆራረጥን በመቃወም እና የፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ስልጣን እንዲለቁ ለመቃወም ብሄራዊ አድማ እንዲደረግ ጠይቋል።

ወደቦች፣ ፓርላማ፣ የድንበር ማቋረጦች እና የጆሃንስበርግ የአክሲዮን ልውውጥ እና ሌሎችም እንደ ቁልፍ የተቃውሞ ሰልፎች ኢላማ እንደሚደረጉ የተቃውሞ መሪው ፓርቲ መሪ ማሌማ አሳውቀው ነበር።

የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤ.ኤን.ሲ) በፈረንጆቹ 1994 የነጮች ጨቋኝ አገዛዝ ካበቃ በኋላ ፓርቲው ከአገሪቱ ብልፅግና እንደተገለሉ በሚሰማቸው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ እና ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን መካከል ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው ይነገራል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply