በደቡብ አፍሪካ ኮሌራ 10 ሰዎች ገደለ

https://gdb.voanews.com/10ABF330-D26C-4F3F-8BF7-AA2BF6E9E784_w800_h450.jpg

በደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ አቅራቢያ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ ቢያንስ 10 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት ትናንት አስታውቀዋል። 

የኮሌራ በሽታ ምልክት የሚታይባቸው 95 የሚሆኑ ሰዎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ወደ ሆስፒታል በመምጣት ላይ መሆናቸውን ወረርሽኙ በተከሰተበት ግዛት የሚገኘው የጤና ቢሮ አስታውቋል። 

ትናንት እሁድ በተደረገ ምርመራ 19 ሰዎች በሽታው እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። 

ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከመጠጣት እንዲቆጠቡ ባለሥልጣናት ጥሪ አስተላልፈዋል። 

የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ለአሥርት ዓመታት ማሽቆልቆልን ካሳየ በኋላ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደገና በመዛመት ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። በ43 አገራት የሚገኝኙና አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን ተመድ አስታውቋል። 

ወረርሽኙ እንደገና ያንሰራራው ድህነት እየጨመረ በመምጣቱ፣ በግጭቶች መበራከትና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ይገልጻል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply