You are currently viewing በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 3  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ያለፍትህ ለወራት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥር 1 ቀን 2014 ዓ….

በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 3 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ያለፍትህ ለወራት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ….

በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 3 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ያለፍትህ ለወራት ታስረው እንደሚገኙ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 3 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራሮች ያለፍትህ ለወራት ታስረው እንደሚገኙ የሰገን ህዝብ እና የአካባቢው ዞን የመኢአድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ገልገሎ ኮይታ ገልጸዋል። በሰገን ህዝብ እና አካባቢው ዞን በደራሼ ወረዳ አሰያ በተባለ ቀበሌ የመኢአድ የወረዳው ስራ አስፈጻሚ የሆነው ሲሳይ ኪታንቦ ከታሰረ አንድ ወር አልፎታል። አቶ ገልገሎ እንደሚሉት አቶ ሲሳይ የታሰረው ለኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ክፈል የተባለውን ገንዘብ አሰራሩ ትክክል ነው ብዬ ስለማላምን አልከፍልም በማለቱ ያለፍትህ ከታሰረ 1 ወር ሆኖታል። ከዚህ በተጨማሪም በሰገን ህዝብ እና አካባቢው ዞን የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ አቶ ከበደ ኦርጋይቶ እና የደራሼ ወረዳ የመኢአድ አባል አቶ ገዛህኝ ሮባዮ ከጥቅምት 12 ቀን 2014 ጀምሮ በፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። የታሰሩት የመኢአድ አባል በመሆናቸው ነው የሚሉት አቶ ገልገሎ በደራሼ ፖሊስ ጣቢያ ያለፍትህ ከ2 ወር በላይ ታስረው ይገኛሉ ብለዋል። “ምን አደረግን?፣ የሰራነው ወንጀል ይገለጽልን?” በሚል ለከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለየወረዳ የፍትህ ተቋማት ብንጽፍም አንቀበልም ስለመባላቸው ተገልጧል። የታሰሩት አመራሮችም ከወራት በፊት በማንነታቸው የተነሳ የመኖሪያ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሲሆን በቀን ስራ ተሰማርተው ከሚሰሩበት ነው ተወስደው የታሰሩት ተብሏል። በመደበኛው የመንግስት አሰራር እና በኮማንድ ፖስቱ መካከል መገፋፋት በመኖሩ ፍትህ እየተዛባ ነው የሚል ቅሬታ ተነስቷል። ከወራት በፊት በአካባቢው ከተፈጸመው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ በፌደራል መንግስትና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ክስ መስርተውብናል ከሚል ቅሬታ ተነስተው ስልጣን በያዙ ከወንጀሉ ጋር ንክኪ ባላቸው አመራሮች የተፈጸመ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply