በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ዞኑን ከሌሎቸች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች በተደጋጋሚ እየተዘጉ ነው ተባለ፡፡በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን ካለው…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ዞኑን ከሌሎቸች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች በተደጋጋሚ እየተዘጉ ነው ተባለ፡፡

በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን ካለው አለመግባባት የተነሳ ዞኑን ከሌሎች ከተሞች የሚያገኛኙ መንገዶች በተደጋጋሚ እየተዘጉ እንደሚገኝ የዞኑ ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፡

በዞኑ በሚገኘው የዳኖ ቀበሌ ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተገኛኘ የቀበሌው ነዋሪ ምለሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ ይህ ችግር መፈጠሩን የቀበሌው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ህዳር 9 /2016 ዓ.ም በጸጥታ ሃይሎች እና በቀበሌው ነዋሪዎች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭትም የተጎዱ እና ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በእለቱ በነበረው ግጭት ፤ከጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች መኖራቸውን የዳኖ ቀበሉ ነዋሪዎች ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

እኛም የተፈጠረውን ጉዳይ ለማጣራት ወደ ኮሬ ዞን ፖሊስ የደወልን ሲሆን የዞኑ ፖሊስ በእለቱ የተፈጠረ ይህን ያህል የተጋነነ ነገር የለም ብሏል፡፡

ነገር ግን በቀበሌው በተደጋጋሚ ከሚነሳው የአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተገናኘ በየጊዜው በአከባቢው ነዋሪ መንገድ እንደሚዘጋ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አራርሶ ነጋሽ ገልጸዋል፡፡

የሚዘጋው መንገድ ደግሞ ዞኑን ከተለያዩ ከተሞች ጋር የሚያገናኝ የፌደራል መንገድ በመሆኑ የሰዎችን የንግድ እንቅስቃሴ የሚገድብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አክለውም በቀበሌው መንገድ በመዝጋት ሲሳተፉ ነበሩ የተባሉ 23 ሰዎች ታስረው እንደነበር የገለጹት ረዳት ኢንስፔክተሩ አሁን ላይ 13 የሚሆኑት ተፈተው የሌሎቹ ጉዳይ በህግ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡

መንገዱን ለማስከፈት በተደረገው ህግን የማስከበር ስራ በጸጥታ ሃይሎች የተወሰደ የተጋነነ ጥቃት አለመኖሩን አንስተዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply