በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ለተፈጸመዉ ጥቃት ተጠያቂዉ ‹‹ፖሌ›› የተባለ የታጠቀ ቡድን መሆኑ ተገለጸ፡፡ለደረሰዉ ጥቃትም እስካሁን ምንም የተሰጠ ምላሽ የለም ተብሏል፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ለተፈጸመዉ ጥቃት ተጠያቂዉ ‹‹ፖሌ›› የተባለ የታጠቀ ቡድን መሆኑ ተገለጸ፡፡

ለደረሰዉ ጥቃትም እስካሁን ምንም የተሰጠ ምላሽ የለም ተብሏል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን የታጠቁ ሃይሎች ሚያዚያ 13 ቀን 2016 በፈጸሙት ጥቃት ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ ሶስት ህጻናትን ጨምሮ አንድ አርሶ አደር መገደላቸዉን ዞኑ አስታዉቋል፡፡

የኮሬ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶሮ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደነገሩን በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ይህንን ጥቃት ሳይፈጽሙ አልቀረም ነዉ ያሉት፡፡

ባለፈዉ ዓመት ህዳር ላይ በኮሬ ማህበረሰብ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን ማህበረሰብ መካከል ዕርቅ ተፈጽሞ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶችም ጥቃቱ እስከተፈጸመበት ቀን ድረስ ስራቸዉን ይሰሩ እንደነበር ነግረዉናል፡፡

‹‹ፖሌ›› የተሰኘዉ የታጠቀ ቡድን ከአንድ ወር በፊት በምዕራብ ጉጂ ዞን የምትገኘዉን ገላና ወረዳ የቀበሌዉን መዋቅር ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩንም ነዉ የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በ16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ቦሬ የምትባል ቀበሌ ላይ ቢሆንም ያለዉ እስካሁን ድረስ ግን ወደ ቦታዉ የገባ ምንም የመከላከያ ሃይል የለም ብለዋል፡፡

ለጥቃቱም የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም ያሉት ሃላፊዉ አሁንም ምንም የተረጋጋ ነገር የለም በማንኛዉም ሰዓት ድጋሚ ጥቃት ሊፈጸም ይችላል ነዉ ያሉት፡፡

የወረዳዉም ሆነ የዞኑ አመራር ወደ ቦታዉ ገብቶ ችግሩን መፍታት የሚችልበት ሁኔታ ምቹ አይደለም ያሉት አቶ ተፈራ፤ዛሬም በቦታዉ ስጋት አለን ብለዉናል፡፡

የኮሬ ዞን አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ፥ ለንጹሐን አርሶ አደሮች ሞት ምክንያት ለሆነው ጥቃት ““በምዕራብ ጉጂ ዞን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና ፀረ-ሰላም” ሲል የጠራቸውን አካላት ተጠያቂ አድርጓል።

እስከዳር ግርማ
ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply