በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን አተዋል ተባለ።ወቅቱ የወባ ስርጭት ከፍተኛ የሚሆንበት በመሆኑ በክልሉ 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የደቡብ ኢትዮ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/AK3l6q9ytQ1B29f04n5znOa0yHv62HBW8NTeQF2uCgYoG4xfI-8E4LkR18AmGM3yql9L1HyHgVLjjXvuzZTo_aVlpVPF8eeHQZ-94YKyELF9VgbrTdiViAGRBeRl1kK1jyWfk5W7V8eRigMrsh3acPc8heCWgbNHhr_gU-1OCBANvIEgOBhrx_r3GhRz_0wP6iYdVFHDF4Kgd5kXsSbjEvTsqDJjRr52sr0w5srSeIJ3AhmtJC-H-PijyrmUiOdN8Ga8SmUcLV3p164l1Y6szyXFl81Xpg5bphOytlrB9L1fsGq2wDO9PsbrWy4fMGF6wK69pTXQdvoW2FOrxCnkyA.jpg

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን አተዋል ተባለ።

ወቅቱ የወባ ስርጭት ከፍተኛ የሚሆንበት በመሆኑ በክልሉ 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ናፍቆት ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በሳምንት እስከ 7 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በወባ በሽታ እየተያዙ እንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም የአካባቢው ማህበረሰብ እንዴት እራሱን ከወባ በሽታ መከላከል እንደሚችል የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

በአከባቢው ላይ ውሀ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስ ስራ እና ማህበረሰቡ አጎበር እንዲጠቀም የማድረግ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ሰዎች የትኩሳት ስሜት ሲሰማቸው በተለይም ህፃናት እና ነፍሰጡሮች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያስተውሉ ወደ ጤና ተቋም ሄደው ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው
የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply