በደቡብ ክልል በ13 ወረዳዎች የሚኖሩ ህዝቦች የኮሌራ ወረርሽኝ ክትባት መውሰዳቸው ተገለጸ፡፡

በደቡብ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ተከስቶ በነበረው የኮሌራ ወረርሽኝ ከ160 በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ጥቂቶች ለሞት መዳረጋቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ክልሉ እየተስፋፋ የመጣውን በሽታ ለመከላከል የውሃ አቅርቦት ከማሟላት ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ክልሉ ከኢትጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት ከ2 መቶ በላይ ቀበሌዎች ክትባቱን እዲያገኙ መደረጉን የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው ሽብሩ ለአሐዱ ገልጸው በዚህም ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ መከተቡን ተናግረዋል፡፡

ተርጫ ከተማና ዙሪያ አከባቢው በስፋት ክትባቱ መሰጠቱን አቶ እንዳሻው ገልፀው ከክትባቱ ጎን ለጎን በአርብቶ አደር አከባቢ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

************************************************************************

ዘጋቢ፡ፀጋነሽ ደረጀ

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply