በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፋርዳ ወረዳ በንጹሀን አማራ ዎች ዘንድ በተፈጸመው ጥቃት ከ38 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ /// አሻራ ሚዲያ…

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፋርዳ ወረዳ በንጹሀን አማራ ዎች ዘንድ በተፈጸመው ጥቃት ከ38 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 13/2013 ዓም ባህር ዳር ///… በጥቃቱ እስካሁን ህይወታቸው አልፎ በወረዳው ዋና ከተማ ቢስቱ ጤና ጣቢያ ውስጥ አስክሬናቸው የገቡ ሟቾች ቁጥር ከ38 በላይ እንደሆነና እስካሁን በህይወት መኖራቸው በውል ያልተለዩ ንጹሀን ግለሰቦች መኖራቸውን ገልጸውልናል፡፡ የጥቃቱ ምክንያት እስካሁን ያልወቀ ሲሆን በጨለማ የንጹሀን ግለሰቦች ቤት እየገቡ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ገልጸውልናል፡፡ በጥቃቱ ህጻናት፤አዛውንትና ሽማግሌዎች ፤የአካል ጉዳተኞች፤እና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ሰለባ መሆናቸውን ምንጫችን ገልጸውልናል፡፡ የጥቃቱን መባባስ ተከትሎ ከሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ሀብት ንብረታቸውን በመተው ነፍሳቸውን ለማዳን በሚል አካባቢውን ለቀው እየተሰደዱ ስለመሆናቸው ነግረውናል፡፡በጉራፈርዳ ከሚኖሩ አማራዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል። ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply