በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ 6500 የሚሆኑ አማሮች ተፈናቀሉ፤ አሻራ ሚዲያ ኅዳር 12 /2013 ዓም ባህር ዳር በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ጉማይዴ የሚባል አዲስ የ…

በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ 6500 የሚሆኑ አማሮች ተፈናቀሉ፤ አሻራ ሚዲያ ኅዳር 12 /2013 ዓም ባህር ዳር በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ጉማይዴ የሚባል አዲስ የወረዳነት ጥያቄን መነሻ በማድረግ ቁጥራቸው ከ6500 በላይ የሆኑ የአማራ ተወላጆች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ ተፈናቅለዋል። በአርባ ምንጭ ከተማ የጋሞ ሕዝብ ድጋፍ እያደረገላቸው የሚገኙት ተፈናቃዮች የአካባቢው ፖሊስ በማፈናቀልና በዘረፋው ተባባሪ ነበር ብለዋል። የግጭት መነሻ ነው ተብሎ በተጠቀሰው የአማሮ ወረዳ አማራዎች የሚኖሩባቸውን ቀበሌዎች በኛ ወረዳ ስር ናችሁ ከዚህ ውጭ የጉማይዴ ወረዳነት ጥያቄ የምትጠይቁ ከሆነ መሬታችን ለቃችሁ ውጡ በሚል ሰበብ የማፈናቀል እርምጃ ወስደውባቸዋል፡፡ በዚህም የደረሰው ጉዳት መጠን ከ6500 በላይ አማራ ተፈናቅሏል፤ አንድም ያልተቃጠለ የአማራ ቤት የለም ሁሉም አመድ ሆኗል፤ ለ55 አመት ያፈሩት ሃበት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤ የደረሰ ማሳቸው ሳይሰበሰብ ወድሟል ለአማራ የወገኑና ተመሰሳሳይ አቋም ያላቸው መጠነ ሰፊ ኮንሶዎች ተፈናቅለዋል (የኮንሶ ዞን አማራን ከደገፋችሁ በሚል የራሱን ወገንም አፈናቅሏል ኮንሶዎች ግን ንብረታቸው አልተነካም) ውስንም ቢሆን የሰው ሂወት ጠፍቷል በአሁኑ ሰአት ምግብ፣ መጠጥ፣ ህክምና ለማግኘት ተቸግረዋል የተላከው የተፈናቃይ ፎቶ የአማራና ከአማራ ጋር ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ኮንሶዎችን ጭምር ያጠቃለለ ነው ተብሏል፡፡ በኮንሶ ዞን መዋቅር የታገዘ የፀጥታ ሀይልና ነዋሪዎች በአማሮ ወረዳ በመዋቅር የታገዘ የፀጥታ ሀይልና ነዋሪዎች ጥቃት አማካኝነት አማራዎች ሸሽተው ወደ አርባ ምንጭ፤ ወደ ሸሌ፤ወደ ቡርጅ ፤ወደ ደራሼ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply