በደቡብ ክልል ከ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

በደቡብ ክልል ከ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
ፈቃድ የተሰጠው ባለሀብቶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለመሰማራት ያቀረቧቸው 218 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተቀባይነት በማግኘታቸው መሆኑን ተገልጿል።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ አስራት አሰፋ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎች ዘመናዊ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ናቸው።
ለባለሀብቶቹ በገጠር 6 ሺህ 825 ሄክታር መሬት፤ በከተማ ደግሞ 40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን አመልክተዋል።
ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ ከታክስና ግንባታ መሬት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ልዩ ማበረታቻዎች መደረጉን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድና የግንባታ መሬት ከወሰዱት ባለሀብቶች መካከል አብዛኞቹ የምርትና አገልግሎት ሥራ ለመጀመር ወደ ግንባታ መግባታቸውን ተናግረዋል።
መሬት ወስደው ወደ ግንባታ የማይገቡ ባለሀብቶችን በመከታተል የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም አቶ አስራት ጠቁመዋል።
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ምርትና አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ከ30 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post በደቡብ ክልል ከ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply