በደቡብ ክልል የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የተሻለ እና አዲስ ሪፎርም እንዲሰራ እንዲሁም በጦር እና በስለት መሳሪያዎች በመታገዝ በንፁሃን ላይ አሰቃቂ ጥቃት እየፈፀሙ ያሉ አካላትን ለህግ…

በደቡብ ክልል የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የተሻለ እና አዲስ ሪፎርም እንዲሰራ እንዲሁም በጦር እና በስለት መሳሪያዎች በመታገዝ በንፁሃን ላይ አሰቃቂ ጥቃት እየፈፀሙ ያሉ አካላትን ለህግ…

በደቡብ ክልል የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የተሻለ እና አዲስ ሪፎርም እንዲሰራ እንዲሁም በጦር እና በስለት መሳሪያዎች በመታገዝ በንፁሃን ላይ አሰቃቂ ጥቃት እየፈፀሙ ያሉ አካላትን ለህግ እንዲያቀርብ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ኢትዮጵያ ደቡብ ምእራብ ቀጠና ሸካ ዞን የኪ ወረዳ፣ የቴፒ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ላለፉት 2 እና 3 ዓመታት ከትሕነግ ጁንታው ጨቋኝ አስተሳሰብ ባልተላቀቁ ባለአደራዎች ተደጋጋሚ አስተዳደራዊ በደል እየደረሰብን ነው፤ የዞን አደረጃጀት ጥያቄያችንም በኃይል እየታፈነብን ይገኛል ሲሉ ተደምጠዋል። ይህን ተከትሎም መንግስት የቴፒ ከተማን በኮማንድ ፖስት እንድትመራ ካደረገ ዓመታት ቢቆጠሩም በታጣቂዎችና በስርዓቱ ውስጥ ባሉ በመንግስት የፀጥታ አባላት ከሚፈፀምባቸው ግድያ፣ አፈና እና ዝርፊያ መታደግ አልቻለም ሲሉ ነዋሪዎች ወቅሰዋል። የደቡብ ክልል በተለይም ደግሞ ቴፒ አዲስና ሁለንተናዊ ሪፎርም ያስፈልጋታል ያሉት ነዋሪዎቹ ሆንተብሎ ግጭት እንዲነሳና የከሃዲው ትሕነግ አላማ እንዲሳካ ሌት ተቀን ተግተው የሚሰሩ አመራሮች አንድን ወገን ለይተው በማስታጠቅ ኢፍትሃዊነትን እያነገሱ ነው ብለዋል። የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት የዞን መዋቅር ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ አያሌ ወጣቶችና ምሁራን በእስር ላይ እንደሚገኙና በእጅጉ ፍትህ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ነዋሪዎች እንዳሉት ታህሳስ 3 እና 4 ቀን 2013 ዓ.ም በታጣቂዎችና በክልሉ የልዩ ሀይል አባላት ተባባሪነት የሰላም በር ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ መስፍን ማሞ፣አቶ ጌታቸው አየለና አቶ አለሙ አምቦ የተባሉ 3 የቴፒ ነዋሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በቆንጨራ እና በገጀራ ተገድለዋል። በተጨማሪም የ25 አባወራ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ስለመቃጠላቸው የተናገረው ወጣት ሚስጥሩ ሲሳይ የሰላም በር ቀበሌ አስተዳደር አቶ መስፍን ማሞ በግፍ የተገደሉት ለኢፍትሃዊ አካሄዱ ባለመመቸታቸው ነው ባይ ነው። ተካ ገ/ማርያም እና በየነች የምትባል ሴትም በገጀራ ተደብድበው ከባድ የአካል ጉዳት ስለደረሰባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሶ ከቃጠሎው ጋር በተያያዘም 4 ጥገት ላሞች፣ ሁለት በሬ፣ፍየል እና ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ በርካታ የቡና ምርት ወድሟል ሲል አክሏል። ከቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply