በደቡብ ክልል የክልል ማዕከል አመራሮችና ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

በደቡብ ክልል የክልል ማዕከል አመራሮችና ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሀገሪቱ ወቅታዩ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ ከተወያዩ በኋላ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ለማበርከት ቃል ገብተዋል።
አመራሮች ለመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ደመወዛቸውን በመለገስ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት በድምሩ 30 ሚሊየን ብር ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እንዲውል ነው ቃል የገቡት።
አመራሮቹና ተቋማቱ በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ማረጋገጣቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

The post በደቡብ ክልል የክልል ማዕከል አመራሮችና ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply