
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀመረ፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ፈተና በ3 ሺህ 782 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
292 ሺህ 769 ተማሪዎችም ፈተናውን እየወሰዱ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ ተናግረዋል፡፡
የፈተና ደህንነት እንዲጠበቅ በሁሉም አካባቢዎች የፈተና ወረቀት ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆይ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ጣቢያችን ቅኝት ባደረገበት የቤንች ሸኮ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ መሆኑን መታዘብ ችሏል፡፡
በቀደሰ ተክሌ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post