በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ አሮጌ ብርሀን ፣3 ቁጥር እና ሙልሙል ያሉ አማራዎች ያለንበት ሁኔታ አስጊ ነው ሲሉ ገለጹ ! የአማራ ሚዲያ ማዕከል ሐምሌ 16 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጉ…

በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ አሮጌ ብርሀን ፣3 ቁጥር እና ሙልሙል ያሉ አማራዎች ያለንበት ሁኔታ አስጊ ነው ሲሉ ገለጹ ! የአማራ ሚዲያ ማዕከል ሐምሌ 16 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጉራፈርዳ አማራዎች ላይ ያተኮረው ጥቃት እየባሰበት መሄዱን ምንጮች ለአሚማ ገለጹ። ሀብት ንብረታችን እየወደመ ነው። ሴት እና ህጻናት ያልለየ ጅምላ ጭፍጨፋ እየደረሰብን ነው ብለዋል። ሀምሌ 10 ቀን ጉራፈርዳ ሙልሙል በሚባለው አካባቢ አንድ የአማራ ተወላጅ ተገድሎ ከብቶቹን እንደዘረፉበት የነገሩን ምንጮች ያለው ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየባሰበት በመሄዱ በሰቀቀን ለመኖር ተገደናል ሰሚም አጥተናል ሲሉ ገልጸዋል። ድረሱንል ስንል ያሉብንን ስጋቶች ለመንግስት አካላት ስንነግራቸው እናንተ መሳሪያ ገዝታችሁ አስመዝግቡ እና ራሳችሁን ተከላከሉ የሚል ምላሽ እንደሚሰጧቸው እና ገዝተው ሲያሳውቁ መሳሪያውን መጥተው ነጥቀው ለታጣቂዎች እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል። ይሄንን ተከትሎ መከላከያ ገብቶ ህይወታቸውን እንዲታደገው ጥያቄ ቢያቀርቡም ጉዳዩ ከክልሉ ልዩ ሀይል በላይ አይደለም የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ለአሚማ ገልጸዋል። የክልሉ ልዩ ሀይልም ሆነ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችም ከታጣቂዎች ድጋፍ እና ከለላ ከመስጠት ያለፈ የአማራ ነዋሪዎች ለሚደርስባቸው ማንነት ተኮር ጥቃት ምንም አይነት ጥበቃ እንደማያደርጉ ገልጸዋል። እስካሁን ከ16 ቀበሌ ወደ ሰላሳ ሺህ አባወራ ተፈናቅሎ ወጥቷል። የ 51 ኢንቨስትር አማራዎች ንብረትም ወድሟል ሲሉ ምንጮች ለአማራ ሚዲያ ማእከል ገለጽዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply