በደቡብ ወሎ-መርከብ ተራራ ላይ ስለ ሀገር እና ስለወገን ሲሉ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የአዴት ወንድማማቾች_ ይበልጣል ኃይሉ አዳምጤ እና አለነ ኃይሉ አዳምጤ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በደቡብ ወሎ-መርከብ ተራራ ላይ ስለ ሀገር እና ስለወገን ሲሉ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የአዴት ወንድማማቾች_ ይበልጣል ኃይሉ አዳምጤ እና አለነ ኃይሉ አዳምጤ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝብ በአሸባሪዎችና ወራሪዎች የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ብሎም ጠላትን ለመደምሰስ በተለያዩ ግንባሮች ከባድ ተጋድሎ እያደረገ መሆኑ ግልጽ ነው። ወራሪዎችን ሲፋለሙም ከአንድ ቤት ሁለት ማለትም አባትና ልጅ ሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ የተሰው እንዳሉት ሁሉ በአዴት ደግሞ ሁለት ወንድማማቾች ተሰውተዋል። የአዴቶቹ ወንድማማቾች ይበልጣል ኃይሉ አዳምጤ እና አለነ ኃይሉ አዳምጤ በደቡብ ወሎ-መርከብ ተራራ ለነፃነታችን ሲሉ ባደረጉት ተጋድሎ የተሰውት። መስዋዕትነታቸውን ተከትሎም የአማራ ህዝባዊ ኃይል/ፋኖ ጀግኖቹ ለተሰውለት ዓላማ እስከመጨረሻው ታምነን እንዘልቃለን ሲል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply