You are currently viewing በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ፣ በሀርቡ ከተማ አስተዳደር በ3 ቀናት ውስጥ ቤታችን እንድናፈርስ መገደዳችን ኃላፊነት የጎደለውና ኃይልን እንደ ብቸኛ አማራጭ የመጠቀም አካሄድ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ከተማ…

በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ፣ በሀርቡ ከተማ አስተዳደር በ3 ቀናት ውስጥ ቤታችን እንድናፈርስ መገደዳችን ኃላፊነት የጎደለውና ኃይልን እንደ ብቸኛ አማራጭ የመጠቀም አካሄድ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ከተማ…

በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ፣ በሀርቡ ከተማ አስተዳደር በ3 ቀናት ውስጥ ቤታችን እንድናፈርስ መገደዳችን ኃላፊነት የጎደለውና ኃይልን እንደ ብቸኛ አማራጭ የመጠቀም አካሄድ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩን ወቅሰዋል፤ ይህ አካሄድ ደግሞ በዘላቂነት ለማንም አይጠቅምም ሲሉ ነው የተናገሩት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ፣ በሀርቡ ከተማ አስተዳደር ከ160 በላይ ነዋሪዎች ከገበሬዎች በመግዛት አብዛኞቹ ከአስር ዓመት ያላነሰ የኖሩበትን ቤት በ3 ቀናት ውስጥ አፍርሱ መባሉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጥር 4/2015 በመዘጋጃ ቤት ለስብሰባ መጠራታችን ተከትሎ ከ100 በላይ የምንሆን ነዋሪዎች ወደ ስብሰባ አቅንተናል ብለዋል። ጥር 4/2015 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ በሚል መጠራታችን ተከትሎ በስብሰባው ብንገኝም ከገበሬዎች ገዝተን በመገንባት ብዙዎቻችን ከአስር ዓመት ያላነሰ የኖርንበት ቤት በ3 ቀናት ውስጥ እንደሚያፈርሱት ነግረውናል ብለዋል። በወቅቱም ከ50 በላይ ታጣቂዎችን አስመጥተው በማስከበብ የስነ ልቦና ጫና ለመፍጠር ሞክረዋል ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ። መሪ መዘጋጃ ቤቱ ከ2 ወር በፊት ነው ከገበሬዎች በመግዛት ወደ ሀርቡ ከተማ ያጠቃለለው የሚሉት ነዋሪዎቹ ከገበሬዎቹ መሬት ገዝተው ሲገነቡ በአመራርነት ሰዎች ውሃ ጭምር እንዲገባልን ማድረጋቸውን ወደ ጎን በመተው አፍርሱ ማለት ግፍ ነው ሲሉ አማረዋል። ቅሬታ አቅራቢዎች የመስተዳድሩ አካላት “የጠሩን በኃይል እንደሚያፈርሱ ለመንገር ነው እንጅ ለመወያዬት አልነበረም” ሲሉ ተናግረዋል። ከአረብ ሀገር ስደተኝነት የተመለሱ እና ከወለጋ የተፈናቀሉ አማራዎች ከተለያዩ አርሶ አደሮች በመግዛት በመገንባት ለረዥም ጊዜ የኖሩበት ቁጥሩ ከ160 በላይ የሚሆን ቤትን በኃይል ለማፍረስ የሚደረገው ጥረት ተገቢ አይደለም ባይ ናቸው። በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ፣ የሀርቡ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን አመዴ በበኩላቸው በህገ ወጥ መልኩ የገነቡ አካላት ስላሉ እና በመመሪያው መሰረት ህግን ማስከበር ግድ ስለሚል ማስፈረሳችን አይቀርም ብለዋል። “እኛን ገድላችሁ ካልሆነ በስተቀር ለማፍረስ አትችሉም”ሲሉ በቁጣ ተናግረዋል የተባሉት ነዋሪዎች ግን ከኃይል ይልቅ ሌላ የመፍትሄ አማራጭ እንዲፈልግላቸው ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply