በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ መካነ-ሠላም ከተማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ላይ ጥቃት ያደረሠው ተጠረጠሪ ግለሰብ በቁጥጥር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ መካነ-ሠላም ከተማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ላይ ጥቃት ያደረሠው ተጠረጠሪ ግለሰብ በቁጥጥር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 16/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ስአት ተኩል አካባቢ በመካነ ሰላም ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ላይ ቦንብ በመጣል ጥቃት የፈፀመው ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር መዋሉን የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው የዞን መርማሪ ቡድን ከቦረና ወዳና መካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅር ጋር በተደረገ የተቀናጀ ምርመራ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ታክቲክ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረ/ኢንስፔክተር ክንዱ ወረቅነህ ተናግረዋል። ጥቃቱ የደረሠው የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ከቅዳሴ በኋላ በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ፀበል ጻድቅ በመቅመስ እያሉ መሆኑን የገለፁት ረ/ኢንስፔክተር ክንዱ ወርቅነህ በተፈፀመው ጥቃትም አንድ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን ህይወታቸው ማለፋንና በ16 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ረ/ኢንስፔክተር ክንዱ ወርቅነህ አያይዘው እንደተናገሩት በደረሰው ጥቃት ተጨማሪ መረጃ እና ምርመራ መቀጠሉን ገልፀው ድርጊቱን ከተለያየ አቅጣጫ በማያያዝ ህብረተሰብን ለማጋጨት የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በከተማው የሚፈፀሙ ተደጋጋሚ ወንጀሎችን ለማስቆም እንደት እየሰራችሁ ነው ? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መልካቸውን እየቀየሩና እየተስፋፉ መምጣታቸው እውነት መሆኑን ገልፀው ይህንን ለማስቆም ህብረተሰቡ በሠላም ወጥቶ እንድገባ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል። ህብረተሰቡ መረጃ በመሆን በተለይም ቤት አከራይ ግለሰቦች የሚያከራዩትን ሰው ሙሉ ማንነት በመለየትና የተለየ እንቅስቃሴ ከታዘቡ ፈጥነው ለፀጥታ ሀይል በማሳወቅና ለፀጥታ መዋቅሩ ተባባሪ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል። ቦረና ኮሙዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply