በደቡብ ወሎ ዞን ከ 6 ቀናት በፊት የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ እያሉ ዋሻ የተደረመሰባቸው ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም ተባለቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎችን ለ…

በደቡብ ወሎ ዞን ከ 6 ቀናት በፊት የኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ እያሉ ዋሻ የተደረመሰባቸው ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም ተባለ

ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎችን ለማውጣት የአካባቢው ማህበረሰብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም፤ እስካሁን ውጤት እንዳልተገኘ የደላንታ ወረዳ አስተዳዳር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የዋድላ ደላንታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አያሌዉ በሪሁን፤ አደጋዉ የደረሰዉ ሌሊት ላይ በመሆኑን ሰዎቹ በየት በኩል እንደገቡ እንኳን ማወቅ ባለመቻሉ ፍለጋዉን አደጋች አድርጎታል ነዉ ያሉት፡፡

የእነዚህ ወገኖች ህይዎት ለማትረፍ የአካባቢዉ ማህበረሰብ እየተረባረበ እንደሚገኝ የነገሩን አቶ አያሌዉ፤ ይሁን እንጅ የሰዎችን ቁጥር በትክክል ማወቅ አልተቻለም ብለዋል፡፡

በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ናዳ የተጫናቸው ባለፈዉ ሃሙት ሌሊት እንደሆነና ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም አብረው ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተነግሯል።

ይሁን እንጅ በአካባቢዉ ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ የዜጎችን ህይዎት ለማትረፍ ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ አካላት እንዲደርስ ለማድረግና መረጃ ለመለዋወጥ ሁኔታዎች ምቹ እንዳልሆኑም ሰምተናል፡፡

በተለያዩ የአለም ሀገራት እንደዚህ አይነት አደጋዎች ሲከሰቱ ቴክኖሊጂን ተጠቅሞዉ ለተጎጂዎች በፍጥነት የመድረሱ ነገር በስፋት ይስተዋላል፡፡

ነገር ግን ለአደጋዉ የተሰጠዉ ትኩረት በቂ ባለመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት እጃቸዉን እንዲዘረጉም ተጠይቋል፡፡

እስከዛዉ ግን በዋሻ ውስጥ ተቀብረው የሚገኙትን ግለሰቦች ለማውጣት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰማርተው በእጅ ቁፋሮ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የደላንታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አያሌዉ ተናግረዋል፡፡

እኛም ለመሆኑ በተለያዩ የክልል ከተሞች አደጋዎች ሲከሰቱ እገዛ የሚያደርገዉ የአዲስ አበባ እስትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለሁኔታዉ ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን ስንል ጠይቀናል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች የሚመጥን ቴክኖሎጂ ባይኖረንም የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

አባቱ መረቀ

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply