በደቡብ ጎንደር ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጣ የሰላም አስከባሪ ኃይል የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ወደ ግዳጅ ቀጠና እያቀና ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በደቡብ ጎንደር ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጣ የሰላም አስከባሪ ኃይል የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ወደ ግዳጅ ቀጠና እያቀና ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ጎንደር ዞን በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጣ የሰላም አስከባሪ የአማራ ሚሊሻዎች ለመከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ሀይል ድጋፍ ለመስጠት ወደ ግንባር ስለመሸኘታቸው የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል። የሚሊሻዎቹ ጉዞ እልህና ወኔ የተላበሰ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከዘር አጥፊው የሕወሓት ቡድን ነጻ የወጡ አካባቢዎችን፣ህዝቡንና ተቋማትን ከሰርጎ ገቦች ጥቃት እንደሚጠብቅ እንዲሁም ህዝቡን ወደ መደበኛ ህይወቱ ይመልሳል ተብሎ ይጠበቃል። በከሃዲው ሕወሓት በጉልበት፣በሴራና በሽፍጥ ተይዘው ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች፣ስወራ፣ማፈናቀልና እስር የሚፈፅምባቸው በርካታ የወልቃይት፣ጠገዴ፣ራያ የአማራ አፅመ እርስቶች በአማራ ልዩ ሀይሎች፣ሚሊሻዎች፣ፋኖዎችና በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መስዋዕትነት ተከፍሎ ነጻ መውጣታቸውና ነዋሪዎችም ደስታቸውን እየገለፁ መሆናቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ከአማራ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጣ ኃይል የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበርና በማረጋጋት ወደ መደበኛ ኑሮው ለመመለስ በሚል ወደ ስፍራው በማቅናት ከፍተኛ ስራ እያከናወነ መሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ተዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply