በደቡብ ጎንደር ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ከ550 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

በደቡብ ጎንደር ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ከ550 በላይ አባዎራዎች ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ድጋፍ የተገኘው “ወገኔ የአረጋውያንና ህፃናት መርጃ ማዕከል” ባስተባበረው የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲሆን በመላው አለም የሚገኙ ተቆርቃሪ ወገኖች በለገሱት ገንዘብ ተፈናቃዮችን መርዳት መቻሉ ተገልጿል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ በተከፈተው ዘመቻ 650 ሺህ ብር እና 500 ብርድ ልብሶች መሰብሰባቸውን የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው አባል ወጣት ታዲዩስ ሲሳይ ለአሻራ ሚዲያ ገልጿል፡፡ በተሰበሰበው ገንዘብም በደቡብ ጎንደር አራት ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው አባወራዎች የሽንብራ እና የአተር ዘር ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡ በመንግስት በኩል ተጎጅዎችን ለመርዳት የተሄደበት ርቀት የጉዳቱን ያክል አይደለም ያሉት ወጣት ታዲዮስ ማህበረሰቡም በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች ለልመና ከመዳረጋቸው በፊት መንግስት ራሳቸውን ሊያቋቁሙ የሚችሉበትን መንገድ ሊቀይስላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply