
በደቡብ ጎንደር ዞን በገብርዬ ብርጌድ ከዶ/ር አምባቸው ሻለቃ በተጨማሪ የብ/ጄኔራል አሳምነው ሻለቃ መመስረቱ ተገለጸ፤ በሌሎች የዞኑ አካባቢም በአስቸኳይ አደረጃጀቱ እንዲጠናከር ተጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ደቡብ ጎንደር ዞን ከሌሎች በተለዬ መልኩ የፋኖ አደረጃጀት እና አባላት ላይ ከአገዛዙ ሰዎች በኩል ግድያን፣ እስር እና መሳደድን ጨምሮ ሁሉም ዓይነት ግፍ እና በደል በተደጋጋሚ የሚደርስበት መሆኑን በመግለጽ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ ቀርቧል። የአሚማ የመረጃ ምንጭ እንደሚሉት የአማራ ህዝብ ከገጠመው የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ብሎም የመኖር ዋስትናውን በማረጋገጥ የሀገር ባለቤትነቱን ለማረጋገጥ የበለጠ መተባበር፣ መደራጀት፣ መቀናጀትና መናበብ ግድ ይለዋል።
Source: Link to the Post