You are currently viewing በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከ90 በላይ ነጋዴዎች ያለምንም ካሳ እና ትክ ቦታ ከሚሰሩበት የግብይት አካባቢ ሊነሱ ነው መባሉን በመግለጽ አካሄዱን ተቃወሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካ…

በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከ90 በላይ ነጋዴዎች ያለምንም ካሳ እና ትክ ቦታ ከሚሰሩበት የግብይት አካባቢ ሊነሱ ነው መባሉን በመግለጽ አካሄዱን ተቃወሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካ…

በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከ90 በላይ ነጋዴዎች ያለምንም ካሳ እና ትክ ቦታ ከሚሰሩበት የግብይት አካባቢ ሊነሱ ነው መባሉን በመግለጽ አካሄዱን ተቃወሙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከ90 በላይ ነጋዴዎች ያለምንም ካሳ ከሚሰሩበት የግብይት ቦታ ሊነሱ መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ገልጸዋል። ይህን የደባርቅ ከተማ አስተዳዳር አካሄድን የተቃወሙት ስራ አጣ ናቸው በሚል ጥቃቅን እና አነስተኛ ከመዘጋጃ ጋር በመናበብ የመስሪያ ቦታ እና ኮንቴነር ከ5 ዓመት በፊት የሰጣቸው ወጣቶች ጥረው ግረው አካባቢውን ካለሙት በኋላ በጨረታ ካለአቅማቸው ከባለሀብት ጋር ጨረታ ግቡ መባላችን ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። በከተማ አስተዳደሩ የተሳሳተ ውሳኔ የተነሳ በደባርቅ ከተማ የከተማው ዋና ገቢያ ላይ የሚገኙት ከ90 በላይ ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆኑ ከ300 በላይ ቤተሰቦች ጭምር ማህበራዊ ህይወታቸው ሊናጋ መሆኑ ተጠቁሟል። ንግድ ፍቃድ ያላቸው ከ90 በላይ ተፈናቃይ ነጋዴዎች በሁለት ማህበር ተደራጅተው እየሠሩ መሆኑ ተገልጧል። ወጣቶቹ እንደሚሉት ያለምንም ትክ ቦታ እና ካሳ፣ ለነጋዴ ማህበረሰቡ ቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ጨረታ እንዲወጣ መደረጉን አውግዘዋል። ከነጋዴ ማህበሩ ውስጥ ከ80% በላይ የሚሆኑት የሴት ነጋዴዎች ሲሆኑ ከነጋዴዎች እየተበደሩ እየሰሩ ነበር፣ ከዚህ በኋላ ለስራ ከብድር እና ቁጠባ የተበደሩትን ገንዘብ የንግድ ቦታቸውን ከተነጠቁ የተበደሩትን ብር መመለስ የማይችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል ተብሏል። የከተማ አስተዳደሩ የስራ እድል ፈጠርኩ ባለ በዓመታት ውስጥ የስራ ቦታችን ነጥቆ ጨረታ በማውጣቱ ቅሬታ ተሰምቶናል በማለት ነጋዴ ማህበሩ እየገለጸ ይገኛል። ከነጋዴ ማህበሩ 50 የሚሆኑት ከ30 ዓመት በላይ ሲሰሩበት የነበረ ሲሆን ሌሎች 40 የሚሆኑት ደግሞ 4 አመት በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን ስራ ከጀመርን 4 አመት የሆነን ቢሆንም ከብድር እና ቁጠባ የተበደርነውን ገንዘብ ገና ሳንመልስ እኛም በበቂ ሁኔታ ሳንቋቋም የስራ ቦታችን ልንቀማ አይገባም ሲሉ ለአሚማ ቅሬታ አቅርበዋል። በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከንግድ ስራቸው የሚፈናቀሉት ነጋዴዎች ለሚመለከተው አካል አቤት ብንልም የሚሰማን አጣን በማለት በምሬት ተናግረዋል። ጨረታው ላይ እንዳንሳተፍም አቅማችን አይፈቅድም ፣ቦታውን ተደራጅተን በማህበር እንድንሰራ ቢፈቀድልን በማለት አቤቱታ ብናቀርብም ሰሚ አጥተናል ይላሉ። ልማቱም ህዝብን ይዞ ስለሆነ ህዝብ አፈናቅሎ የሚመጣ ልማት ስለሌለ በአስቸኳይ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል። ከተማ አስተዳደሩ ገብሬ፣ ሁላገር እና ጓደኞቻቸው የሞባይል ሽያጭ እና ጥገና ማህበር በስሩ 40 አባላት ያሉት አደረጃጀት ላቀረበው ቅሬታ ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ በደብዳቤ ስለመስጠቱ ወጣቶች ተናግረዋል። አሚማ በሰሜን ጎንደር ዞን ለደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ለአቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ቢደውልም የሚጠራ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply