በደባርቅ ከተማ ከቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተከስቶ ነበር የተባለውን የጸጥታ ችግር ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በደባርቅ ከተማ ከቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተከስቶ ነበር የተባለውን የጸጥታ ችግር ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ሚያዝያ 20/2014 ከረፋዱ ሶስት ሰዓት ገደማ በከተማዉ ቀበሌ 01 በምትገኘዉ የጎጢት ማርያም ቤተክርስቲያን የተከሰተዉን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ የተፈጠረዉ የፀጥታ ችግር እንደነበር ተገልጧል። ይህን ተከትሎም የሰው ህይወት ማለፉንና የተቃጠሉ መስጊዶች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። የደባርቅ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን “በአካባቢዉ ወጣቶች፣ በሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሃይል፣ በአካባቢዉ ሚሊሻና መላዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረገዉ ብርቱ ጥረት ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ተመልሷል፤ እሳቱም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል” ማለቱ ይታወሳል፡፡ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር ከአካባቢዉ ህዝብ ጋር በመቀናጀት አጥፊዎችን ለማሳዎቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ስምሪት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልጧል። አካባቢዉ ለጠላት ቅርብ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለጠላት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ህዝባችን አብሮ የመኖር እሴቱን ለማጠናከር አጥፊዎችን በህግ እንዲጠየቁ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply