You are currently viewing በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ  ጭስ አልባ ከሰል መመረቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም …         አዲስ አበባ ሸዋ በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የሲ…

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጭስ አልባ ከሰል መመረቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የሲ…

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጭስ አልባ ከሰል መመረቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ፈቃዱ እንግዳ እንደተናገሩት ፤ ከቆሻሻ የሚሰራ ጭስ አልባ ከሰል ማምረት መቻሉን ገልፀዋል። ምርቱ ከፕላስቲክ ፣ ብርጭቆ እና የብረት ተረፈ ምርት ዉጪ የመጸዳጃ ቤት ፣ የእንስሳት ጽዳጅ እንዲሁም ማንኛውንም ቆሻሻዎችን ለምርቱ እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል። በ 2012 ዓ.ም የተጀመረዉ ፕሮጀክቱ ላለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዉበታል ብለዋል። ምርቱ በገበያ ላይ ካለዉ የእንጨት ከሰል የተሻለ መሆኑን ያነሱት የፕሮጀክቱ ባለቤት ፤ ከዚህ ቀደም ከቆሻሻ ከሚመረተዉ ጭስ አልባ ከሰል በተለየ ለማህበረሰቡም ሆነ ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መጠን ተዘጋጅቷል ብለዋል። ሆኖም ይህን ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለመለወጥ እና በስፋት ለማምረት ግን አመቺ የስራ ቦታ ማጣት እና የማሽነሪ አለመሟላት እንዳጋጠማቸዉ ገልጸዋል። የስራ ቦታን በሚመለከትም ከከተማ አስተዳደሩ ቦታ የተጠየቀ ቢሆንም ፤ አስተዳደሩ ቦታ የሚያቀርበዉ እንደ አንድ ባለሃብት ተመዝገበዉ አስፈላጊ መስፈርቱን ኳሟሉ እንደሆነ እንደተነገራቸዉ መምህሩ ገልፀው ይህን ለሟሟላት ግን አቅሙ እንደሌላቸዉ ተናግረዋል። ፕሮጀክቱን ለመስራት በደብረማርቆስ ከተማ የመጸዳጃ ቤት ቆሻሻ መጣያ አመቺ ቦታ አለመኖሩ እና በአዲስአበባ (ቆሼ) በተከሰተዉ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች መነሻ ምክኒያት እንደሆናቸዉ መምህር ፈቃዱ ጨምረው ስለማብራራታቸው ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply