You are currently viewing በደብረብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለምግብ የሚሆኑ እና ለተፈናቃዮች የሚያገለግሉ ልብሶችን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ነበር የተባለው ኤርሚያስ መኩሪያ በመከላከያ ሰራዊት እና…

በደብረብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለምግብ የሚሆኑ እና ለተፈናቃዮች የሚያገለግሉ ልብሶችን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ነበር የተባለው ኤርሚያስ መኩሪያ በመከላከያ ሰራዊት እና…

በደብረብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለምግብ የሚሆኑ እና ለተፈናቃዮች የሚያገለግሉ ልብሶችን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ነበር የተባለው ኤርሚያስ መኩሪያ በመከላከያ ሰራዊት እና በደህንነት አባላት ታፈነ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቤቱ በመውጣት ወደ መርካቶ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት የመከላከያ ኮማንዶዎችና የደህንነት አባላት አፈና እንደፈፀሙበት የአይን እማኞች ገልጸዋል። ኤርሚያስ ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪናውንም ከደህንነት አባላት አንዱ እየነዳ የወሰደው ሲሆን እየሆነ ያለውን ለባለቤቴ ላሳውቅ ሲል ጥያቄ ቢያቀርብላቸውም ሊፈቅዱለት እንዳልቻሉ እና ነገ ትደውላለህ የሚል ምላሽ እንደሰጡት ለማወቅ ተችሏል። ኤርሚያስ መኮንን በዛሬው ዕለት ወደ መርካቶ ሲጓዝ የነበረው ከወለጋ ተፈናቅለው በደብረብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለምግብ የሚሆኑ እና ለተፈናቃዮች የሚያገለግሉ ልብሶችን ለመግዛት እየተጓዘ በነበረበት ወቅት መሆኑን ታውቋል። ኤርሚያስ መኩሪያ እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም ሲል ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply