በደብረ ማርቆስ ከተማ በቤት ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የነበሩ ከ9ሺ በላይ የቤት መስሪያ ቦታ ፈላጊዎች እጣ አወጡ፡፡ ባህርዳር:- ሚያዚያ 22/2014 ዓ.ም…

በደብረ ማርቆስ ከተማ በቤት ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የነበሩ ከ9ሺ በላይ የቤት መስሪያ ቦታ ፈላጊዎች እጣ አወጡ፡፡ ባህርዳር:- ሚያዚያ 22/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በደብረ ማርቆ ከተማ በቤት ህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የሚጠበቅባቸውን ካሳ ከፍለው የቤት መስሪያ ቦታ ለመቀበል ሲጠባበቁ የነበሩ4መቶ 97 ማህር ማለትም 9ሺ 2መቶ 95 የማህበር አባላት ያላቸው በማህበር ተወካያቸው አማካኝነት እጣ አውጥተዋል፡፡ የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት ለሆነው ቤት ባለቤት ለመሆን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት በዕጣ ማውጣት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ይትባረክ አወቀ በከተማ አስተዳደር ደረጃ በአንዴ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ቤት ፈላጊ ያስተናገድንበት ይህ የመጀመሪያው በመሆኑ ትክክለኛ ቤት ፈላጊውን ለማጣራት ከወቅታዊ የሃገራችን የፀጥታ ችግር ጋር ተያዞ ጊዜ ፈጅቷል፣በዚህም መጉላቶች ስለነበሩ ይህን ታግሳችሁ የቤት ባለቤት ለመሆን ዕጣ ስላወጣችሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በ2መቶ 80 ሄክታር መሬት ላይ በማህበር የተደራጁ 9ሺ 2መቶ 95 የማህር አባላትንና ቦታው የተወሰደባቸው የአርሶ አደር ልጆችን ጨምሮ 10ሺ 6መቶ 64 ቦታ በመሸንሸን እና በ36 ብሎክ በመክፈል ለቤት ፈላጊዎች ለማስረከብ ስራዎች አልቀው የእጣ ማውጣት ሲነ-ስርዓት መካሄዱን የገለፁት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የኮንስራክሽን ዘርፍ ም/ መምሪያ ኃላፊ አቶ አወቀ አለሙ በቀጣይ በእጠው መሰረት ቦታ የማስረከብ ስራው ይከናወናል ብለዋለ፡፡ ለዓመታት ሲጠብቁት የነበረውን የቤት መስሪያ ቦታ ይሰጠን ጥያቄ መፍትሄ በማግኘታቸውና እጣ በማውጣታቸው መደሰታቸውን አስተያይታቸውን የሰጡ የማህር አባላት ገለጹ፡፡ Via, Debre Markos City Communication ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply