በደብረ ማርቆስ ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ በ48 የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደረሰ

በደብረ ማርቆስ ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ በ48 የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተነሳ የእሳት አደጋ በ48 የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አጃናው አዲስ  የእሳት አደጋው የደረሰው በጉልት ገበያ አዳራሽ መሆኑን ተናግረዋል።

በአደጋው በንግድ ሱቆቹ ውስጥ የነበሩ አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ጠቅሰዋል።

የአደጋው መንስኤና የወደመው ንብረት ግምት በፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝ  የጠቆሙት ዋና ኢንስፔክተሩ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አመልክተዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ተሳትፎ የእሳት አደጋው ወደ ሌሎች ሱቆች ሳይዛመት መቆጠጣር እንደተቻለ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በደብረ ማርቆስ ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ በ48 የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደረሰ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply