በደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለዉ የሚገኙ ከ26ሺህ በላይ ዜጎች ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ናቸዉ ተባለ፡፡የመንግስት ድጋፍ ወጥ አለመሆንና በፀጥታው ምክንያት ከሌሎች ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ መቋረጡ…

በደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለዉ የሚገኙ ከ26ሺህ በላይ ዜጎች ከፍተኛ ችግር ዉስጥ ናቸዉ ተባለ፡፡

የመንግስት ድጋፍ ወጥ አለመሆንና በፀጥታው ምክንያት ከሌሎች ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ መቋረጡ ችግሩን እንዳባባሰው ሰምተናል፡፡

በበደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘዉ ቻይና ካምፕ ጊዚያዊ መጠለያ አስተባባሪ አቶ ጌትዬ ደርቤ ተፈናቃዮቹ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የሰባዊ እርዳታ በመደበኛነት አለመቅረብና ወቅታዊ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ደግሞ ችግሩን ከፍ እንዳደረገዉ ተናግረዋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ጊዚያዊ መጠለያ ካምፖች ዉስጥ ተጠልለዉ የሚገኙ ወገኖች አብዛኞቹ ከወለጋ አካባቢ ተፈናቅለዉ የመጡ እንደሆኑ ሰምተናል፡፡
ዜጎቹ አሁን ላይ የሰዉ እጅ ከመጠበባቃቸዉ በፊት አርሰዉ እራሳቸዉን ብቻም ሳይሆን ወገኖቻቸዉን የሚመግቡ ነበሩ፡፡

የምንጊዘ ህልማቸዉም ወደ ቄያቸዉ ተመልሰዉ እራሳቸዉን መቻል ነዉ፤ ያ ግን እስካሁን ባለመሆኑ አዲስ አመትን በአሳዛኝ ሁኔታ ለማሳለፍ ተገደዋል ይላሉ አቶ ጌትዬ፡፡

አቶ አንተነህ ገብረ እግዚሓብሄር ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የስነ ህዝብ ባለሙያና የመጠለያ ካምፖች አስተባባሪ ናቸዉ፤ እርሳቸዉ በተፈናቃዮቹ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በሰጡን ማብራሪያ በመንግስት የሚደረገዉ ድጋፍ በመደበኛነት እየመጣ አይደለም በግለሰቦች የሚቀርበዉ ደግሞ በፀጥታዉ ምክንያት ተቋርጧል ነዉ ያሉት፡፡

ከምግብ አቅርቦት ችግሩ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በማእከሎች ዉስጥ የኮሌራ በሽታ እንደተከሰተ ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነዉ፡፡
ይሁን እንጅ አሁን ላይ ስጋቱ ቢኖርም በመጠለያ ካምፖች ዉስጥ አልተከሰተም ብለዋል፡፡

ዛሬ ላይ የሚጎርሱት የሚለብሱትና የሚጠለሉበት አጥተዉ የሰዉን እጅ ከመጠባበቃቸዉ በፊት ከእርሳቸዉ አልፎ ለተቸገሩ የሚተርፉ ወገኖች ነበሩ፡፡

በዓላት ሲመጡም በሞቀ ቤታቸዉ ሆነዉ አዉዳመትን በደስታ የሚያሳልፉ ዜጎች እንደነበሩ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸዉ ቆይታ መናገራቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

አሁን ላይ በደብረ ብርሃን ሶስት መጠለያ ካምፖች ዉስጥ ከ26 ሺህ በላይ ዜጎች የሰዉ እጅ በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ፡፡

በተለይም የምግብ አቅርቦት መበደበኛነት አለመኖር ደግሞ ዋነኛዉ ችግር ነዉ ፡፡ እናም አቶ አንተነህ ቀጣይ ጊዚያት የከፉ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል፡፡
እናም ለእነዚህ ወገኖች ከመንግስት በተጨማሪም ሁሉም ዜጋ እጁን እንዲዘረጋ ወገናዊ ጥሪ ተላልፏል፡፡

በአባቱ መረቀ
መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply