በደብረ ታቦር ከተማ ቴዎድሮስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ መሠናዶ ት/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት 1028 ተማሪዎች መካከል 4 ተማሪዎች ከፍየኛ ውጤት…

በደብረ ታቦር ከተማ ቴዎድሮስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ መሠናዶ ት/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት 1028 ተማሪዎች መካከል 4 ተማሪዎች ከፍየኛ ውጤት…

በደብረ ታቦር ከተማ ቴዎድሮስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ መሠናዶ ት/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት 1028 ተማሪዎች መካከል 4 ተማሪዎች ከፍየኛ ውጤት አስመዘገቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደብረ ታቦር ከተማ ቴዎድሮስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ መሠናዶ ት/ቤት እንዳስታወቀው:_ 1ኛ. ተማሪ ቴዎድሮስ አገኘሁ ፈንቴ ያመጣው ውጤት 625 2ኛ. ተማሪ አቢይ ብሩክ ቢሆነኝ ያመጣው ውጤት 609 3ኛ.ተማሪ ብስራት አዲስ ሹሜ ያመጣው ውጤት 604 4ኛ. ይትባረክ አስናቀው መብሬ ያመጣው ውጤት 602 በአጠቃላይ 4 ማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል። በሀገራችን በተደጋጋሚ በሚፈጠሩ ወቅታዊ ክስተቶች ምክንያት ፈተናው ሲራዘም በመቆየቱ በተማሪዎች ላይ ያሳደረው ጫና ቢኖርም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመጠቀምና በቂ ዝግጅት በማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልፀዋል። ተማሪ ብስራት አዲስ ሹሜ እንደገለፀው በኮቢድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ቤታችን ተዘግቶ ቢቆይም እኔ ግን አንድ ቀን እንደምንፈተን ተስፋ በማድረግ ቀንም ሆነ ማት ጊዜየን በፕሮግራምና በአግባቡ በመጠቀም ለዚህ ውጤት መብቃቱን ገልጿል። ተማሪ ይትባረክ አስናቀው መብሬ ያስመዘገበው ውጤት 602 ሲሆን ይህ ዓመት ሀገራችን በተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ችግሮች ፈተና ውስጥ የገባችበትና እሱንም በከፍተኛ ውጤትና የድል ድምቀት ያለፍንበት ወቅት ላይ ሆነን ፈተና የወሰድንበት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግሯል። የሁሉም ተማሪ የጥናት ስልት የተለያየ ሲሆን ተማሪዎች በሚያጠኑበት ጊዜ መቼ?የትና? እንዴት? ማንበብ እንደሚገባቸው አስተውሎት በመስጠት ማጥናት እነደሚገባቸው ለቀጣዮቹ ተፈታኝ ተማሪዎች እመክራለሁ ብሏል። የደብረ ታቦር ከተማ ቴዎድሮስ አጠቃላይ መሰናዶ ት/ቤት ር/መምህር አቶ ካሳየ ጠጋየ እንደገለፁት በት/በታችን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ተማሪዎች በሁሉም የት/ቤት መምህራንና አሰተዳደር ሰራተኞች ደረጃ ተጠባቂዎች እንደነበሩ ገልፀው በመደበኛ የመማር ማስተማር መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ቢሆን ኖሮ ካስመዘገቡት ውጤት በላይ እንደሚያስመዘግቡ አልጠራጠርም ብለዋል። አጠቃላይ በደፊት የሚፈተኑትና በዝግጅት ላይ ያሉ ተማሪዎቻችን የስነ ልቦና ዝግጅት ካለ የትኛውም ፈተና ከፊታችን ላይ በጋረጥ የማንሻገረው ወንዝና የማነወጣው ተራራ የለም በማለት ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለተማሪዎቻቼው አያይዘው ገልፀዋል። በመጨረሻም የቀጣይ ሀገር ተረካቢና እንቁ ልጀች ለዚህ ውጤት ላበቋቸውን ወላጆች፣ መምህራንና ለት/ቤቱን ስታፍ ሠራተኞች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ደብረ ታቦር ኮሙኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply