በደብረ ኤልያስ ፋኖን በማገዝ የተጠረጠሩ ገዳማት በጥይት ተደበደቡ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 12/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ ‘ፋኖን ታግዛላችሁ፣ ለፋኖ ትጸልያላችሁ” የተባለው የምራተ ብፁዓን አቡነ ተክለ ኃይማኖት አንድነት ገዳም ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ተኩስ ተከፍቶበት እንደነበር ተገልጧል። የንስር ዘገባ እንዳመለከተው በተኩሱም ምህላ ላይ የነበሩ ገዳማውያን አባቶች የተረበሹና መንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸው የተስተጓጎለ ይሁን እንጅ የሰው ሕይወት አልጠፋም ተብሏል። የደብረ ኤሊያስ ገዳም አባቶች፣ እናቶች እና ምዕመናን ላይ ከወራት በፊት ስርዓቱ ባሰማራው ጦር በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች በአሳዛኝ መልኩ መገደላቸው እና ተከታታይ ትንኮሳ እየተደረገባቸው መሆኑ ይታወቃል።
Source: Link to the Post