በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምርጫ የተሸነፉት ሞይሴ ካቱምቢን ቤት ወታደሮች ከበባ ውስጥ ማስገባታቸው ተነገረ፡፡በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁትን…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/VIkB3WOW2ykeMwWFV5upx0HlXl3Uxs3IZScvOJExKGWCUxU-W793fQwhMYvNu4ouQUyafuhTBCa8cOrn4fy-qeWgUhT8qyVqoeYJJy_lohS6cykC1gU8t3R_D44XGZMNLcG7HQAAQUBw53IhP2vK5mb6X2HurO_wTm9phSI3_qcZr1_y9rSk3bkSg6vxDqoVH9FMK0QV5F_Jvwdfer-KBpeVNJ-0uTkXfsKhVWq5J0SHiUiNiVrCNXO4ZZ8RmUauAupsXrYtvkZE0OxzFWY1Re9mfH_IKfYPP0ms86Fm1WcsWHi9avuvV0VRUji0hqFSCVjiLLf9aEvVReLd7u8sjw.jpg

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምርጫ የተሸነፉት ሞይሴ ካቱምቢን ቤት ወታደሮች ከበባ ውስጥ ማስገባታቸው ተነገረ፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁትን የሞይሴ ካቱምቢን ቤት የፀጥታ ሀይሎች ለአጭር ግዜ ከበባ ውስጥ አስገብተውት ነበር ተብሏል፡፡

ሰኞ ዕለት በደቡብ ካታንጋ ግዛት ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እንዳይወጣ ተከልክሎ እንደነበር ቃል አቀባዩ ሄርቬ ዲያኬሴ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ የፀጥታ አካላቱ በአከባቢው አስተዳዳሪ ትዕዛዝ ከቦታው ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

ተቃዋሚውም ካቱምቢ ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ የፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቱሺኪዴን ድል ሲያጣጥሉት መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የምርጫ ውጤቱንም በተመለከተ በሶስተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው ማርቲን ፋዩሉን ጨምሮ አምስት የታቃዋሚ መሪዎች የምረጫውን ውጤት በመቃወም የተቃውሟ ሰልፍ ጠርተዋል፡፡

ከካቱምቢ ቤተሰቦች አንዱ ለፈረንሳዩ RFI የዜና ወኪል እንደተናገሩት “ቤቱ በከፍተኛ ወታደሮች ተከቦ”ነበር ብሏል፡፡

ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝዳንት ቲሺኪዴ 73 በመቶውን ሲያሸንፉ ካቱምቢ 18 በመቶ እንዲሁም ፋዩሉ 5 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል ሲል የምርጫ ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡

ከምርጫው በኋላ በተፈጠረ ሁከት ወደ 20 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply