በዳሰነች ወረዳ በ12 የመጠለያ ጣቢያዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የመጠጥ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ተባለ፡፡በመጠለያው ጣቢያ በቤተሰብ ከ79 ሺኅ 8 መቶ በላይ ዜጎች እንደሚገኙ የዞኑ አደጋ ቅነሳ…

በዳሰነች ወረዳ በ12 የመጠለያ ጣቢያዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የመጠጥ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ተባለ፡፡

በመጠለያው ጣቢያ በቤተሰብ ከ79 ሺኅ 8 መቶ በላይ ዜጎች እንደሚገኙ የዞኑ አደጋ ቅነሳ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ መሙላትን ተከትሎ በዳሰነች ወረዳ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምንያት በ12 የመጠለያ ጣቢያዎች ላይ በቤተሰብ ከ79 ሺኅ 8 መቶ በላይ ዜጎች ተጠልለው እንደሚገኙ የዳሰነች ወረዳ አደጋ ቅነሳ እና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሃላፊ ኡስማን ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

የመጠለያው ጣቢያ ከኦሞ ወንዝ እርቀት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ሃላፊው በመጠለያው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የመጠት የውሃ እጥረት መኖሩን ገልጸዋል፡፡

በፌ.ደ.ራ.ል መንግስት እና በክልሉ የምግብ እና የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር አሁንም በቂ አለመሆኑን ጠቁሟል፡፡

በድጋፍ ከተገነልኘው ለ1 ወር ያክል የሚበቃ እህል መኖሩን ተናረዋል ቸግሩንም ለመፍታት የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ጥረቶችን መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የኦሞ ወንዝ መሙላትን ተከትሎ በመጠለያ ጣቢያው የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን ገልጸዋል።

በእሊኒ ግዛቸው

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply