You are currently viewing በዳኞች አለመሟላት ምክንያት በተደጋጋሚ ፍ/ቤት እየተመላለሱ ያሉት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 14…

በዳኞች አለመሟላት ምክንያት በተደጋጋሚ ፍ/ቤት እየተመላለሱ ያሉት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14…

በዳኞች አለመሟላት ምክንያት በተደጋጋሚ ፍ/ቤት እየተመላለሱ ያሉት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ ለህዳር 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በዳኞች አለመሟላት ምክንያት በተደጋጋሚ ፍ/ቤት እየተመላለሱ ያሉት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ ዛሬ ህዳር 14/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ጠበቃ ታለማው እንዳሉት ታዲዎስ ታንቱ ፍ/ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳኞች በብይኑ ላይ ተጨማሪ የምናዬውና ያልተሟላ ነጥብ አለ በማለት ለፊታችን አርብ ህዳር 16/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከአሁን ቀደም የክስ መቃወሚያ ቀርቦ ውድቅ በማድረግ ብይን የተሰጠ መሆኑን ተከትሎ ዐቃቢ ህግ ያቀረባቸውን 5 ክሶች የአመራር ሂደትን ለመበዬን በሚል ነው ቀጠሮው የተሰጠው ብለዋል ጠበቃ ታለማው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply