በዳያስፖራው የተፈጠረው መነሳሳትና የአንድነት ስሜት ቀጣይነት እንዲኖረው ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በዳያስፖራው የተፈጠረው መነሳሳትና የአንድነት ስሜት ቀጣይነት እንዲኖረው ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ:: የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ የዳያስፖራዉ ማህበረሰብ በሀገር ልማትና ዕድገት ለማሳተፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ገልጿል፡፡
የዳያስፖራ የምክክር መድረክ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደበት ወቅት የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠላማዊት ዳዊት እንዳሉት ዳያስፖራው አባላት በንግድና ኢንስትመንት፣ በዕውቀት ሽግግር፣ በሬሚታንስና በሌሎች ወሳኝ የሀገር ልማት ጉዳዮች እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ለማጠናከር የተከናወኑ
ተግባራት አበረታች ናቸዉ፡፡

ዳይሬክተሯ ዳያስፖራው በአገራዊ ጉዳዮች የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያለምንም የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ለማገልገል የሚያስችል ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ዳያስፖራው በትላልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ አሻራቸውን በማኖር ረገድ በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

እንዲሁም የኮሮና ወረርሽኝን ሥርጭት ለመግታት በገንዘብና በዓይነት ከፍተኛ ሀብት አሰሰባስበው ለወገን ደራሽነታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በትግራይ ለተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻና በሂደቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል። መረጃዉን ያገኘነዉ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃላቀባይ ጽ/ቤት ነው::

Source: Link to the Post

Leave a Reply