“በዳዳ ገመቹ የድለላ ባለሙያዎች” አለም አቀፍ የቤት ግብይይት ይፈፅሙ ዘንድ አመቺ አሰራርን ይዤ መጥቻለሁ አለ።

በዳዳ ገመቹ የድለላ ባለሙያ ስራ ድርጅት ከ 26 ዓመታት ቆይታ ሃገር ውስጥ የከፈተውን ኢትዮ ሌግዤሪ ሆምስ ቢሮ በኔትዎርክ ትስስር አሜሪካን ሃገር አስቀድሞ ከከፈተው ኢትዮ ሌግዤሪ ሆምስ ቢሮው ጋር የገበያ ትስስር ማስጀመሩን በይፋ አስታወቀ።

ድርጅቱ በኔትወርክ ትስስር ብቻ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በኢንተርኔት አጋዥነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቤቶችን እንዲገዙ፣ የቤቶቹን ስፋትና የተሰሩበትን ማቴሪያል አድራሻቸውንም ጭምር በኢንተርኔት በማየትና በኢንተርኔት የክፍያ ስርዓት ብቻ ቤት ገዝተው የቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሰራር ይዤ መጥቻለሁ ብሏል።

በአሜሪካ አሌክስአንድሪያ ከተማ  EthioLuxury Homes በሚል ስራ የጀመረው ድርጅታቸው፤
በዚህ አገልግሎቱ ኑሯቸውን ባህርማዶ ያደረጉ ወገኖቻችንን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው እድል እና አጋጣሚ በመፍጠር ፈጥረዋል።

ዲያስፖራው ህብረተሰብ ከባንኮች ጋር የሚሰሩበትን ሁኔታዎች ማመቻቸትና : ገዢዎች ከባንኮች ጋር  መስራት እንዲችሉ ያማክራል፣ ቤቶች ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ የግብይት ስርዓት እንዲኖራቸው ማድረግ፤ የቤት ዋጋዎችን ግልጽ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ በማዋቀር የበኩሉን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኢትዮ ሌክጀሪ ሆምስ ሕንጻና የተለያዩ ንብረቶችን  ያስተዳድራል።

The post “በዳዳ ገመቹ የድለላ ባለሙያዎች” አለም አቀፍ የቤት ግብይይት ይፈፅሙ ዘንድ አመቺ አሰራርን ይዤ መጥቻለሁ አለ። appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply