በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡባዊ ክፍል ኪቩ ግዛት አቅራቢያ የአውሮፕላን አደጋ ተከስቶ የሶስት አብራሪዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፡፡

አንድ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አነስተኛ አውሮፕላን ከኪንሻሳ በስተ-ምሥራቅ አቅጣጫ 1 ሺ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው ምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ኪቩ ከተማ አቅራቢያ ከካቩሙ የአየር ማረፍያ ተነስቶ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አደጋ እንደደረሰበት የኮንጎ አየር መንገድ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቪዬሽን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ማዕድናትን እና ሌሎች ዕቃዎችን የሚያጓጉዘው ኤል 410 አነስተኛ አውሮፕላን አደጋ ከተከሰተበት በኋላ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቀይ መስቀል የመጀመሪያ እርዳታዎችን እንዳደረገ በማንሳት አደጋውን አስከፊ እና ዘግናኝ ያልተጠበቀ ክስተት ነው ሲል ገልጾታል፡፡
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡባዊ ግዛት የኪቩ አስተዳደር ባለሥልጣናት እና ባለሙያዎች በበኩላቸው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋውን እያጣራን ነው የደረስንበትን እናሳውቃለን ብለዋል፡፡
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

ቀን 10/10/2013
አሐዱ ራድዮ 94.3

The post በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡባዊ ክፍል ኪቩ ግዛት አቅራቢያ የአውሮፕላን አደጋ ተከስቶ የሶስት አብራሪዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply