በዴንቨር አምስት ሰዎችን ገድሏል የተባለው ሰው ሟቾቹን ሲከታተላቸው ነበር ተባለ

ከትናንት በስቲያ ሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ግዛት ዴንቨር አካባቢ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር፣ አምስት ሰዎችን ተኩሶ በመግደል የተጠረጠረው ሰው አንዳንዶቹ ለመግደል ይፈልጋቸው የነበሩ ሰዎች መሆናቸውን ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

ተጠርጣሪው አንድ ፖሊሲ ላይ ተኩሶ ያቆሰለ መሆኑን ሲገልጽ ፖሊሱም በአጸፋው በተኮሱት ጥይት መሞቱ ተመልክቷል፡፡ 

ተጠርጣሪው የ47 ዓመት ልጅ ሊንድን ጀምስ መክሎይድ ሟቾቹን ይከታተላቸው እንደነበር በፖሊሲ ይታወቅ የነበረው ቢሆንም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግን አለመገለጹ ተነግሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply