#በድህረ ወሊድ ወቅት #ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፡- በቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ ወቅት በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠዉን ትምህርት መከታተል እናቶች ከወለዱ ቡኋላ ባለማወቅ የሚፈጽሙትን ተግ…

#በድህረ ወሊድ ወቅት #ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፡-

በቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ ወቅት በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠዉን ትምህርት መከታተል እናቶች ከወለዱ ቡኋላ ባለማወቅ የሚፈጽሙትን ተግባር ከማድርግ እንዲቆጠቡ ያደርጋል፡፡
እናቶች ከወለዱ ቡሃላ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድርግ አለባቸዉ? ስንል የጤና ባለሙያ አነጋግረናል፡፡

ባለሙያዉ አቶ #መዝገቡ ጫንያለዉ የማህበረሰብ ጤና ጥበቃ ባለሙያ ናቸዉ፡፡
ባለሙያዉ እንደሚሉት ከሆነ በቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ ወቅት ለእናቶች የሚሰዉ የጤና ትምህርት እናቶች ለሚወልዱት ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ጠቃሚ ነዉ ይላሉ፡፡

#ለመሆኑ ጡት ሲያጠቡ እናቶች እንዴት ነው ማጥባት ያለባቸዉ?

የእናት ጡት ወተት በአለማችን ላይ ያለ ዉድ ምግብ ከመሆኑም በላይ የእናት ጡት ወተት ከማንኛዉም በሽታ የሚከላከል ሲሆን ለተወለደዉም ልጅ የዓዕምሮ እድገት ወሳኝ ነዉ ብለዋል ባለሙያው፡፡

በተጨማሪም የመጀመሪያዉ የእናት እና ልጅ ትዉዉቅ የሚጀምርዉም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነዉ ይላሉ ባለሙያዉ አቶ መዝገቡ ጫንያለዉ፡፡
እናቶች ከራሳቸዉ ጡት ዉጭ ለልጆቻቸዉ የሚሰጡ ከሆነ ለአንጀት ቁስለት ፤ለሳንባ ምች ፤ለተቅማጥ ፤ ለትኩሳት እና ለተለያዩ ኢንፌክሺኖች ሊጋለጡ ይችላሉም ተብሏል፡፡

#እናቶ ጡት በሚያጠቡበት ወቅት ምን አይነት ጥንቃቄን ማድርግ አለባቸዉ?

እናቶች ጡት በሚያጠቡበት ወቅት ልጁን በጎን ማስቀመጥ አይመከርም እንዲሁም የጡት ጫፉን በደንብ እንዲጎርስ ማድርግ አለባቸዉ የሚሉት ባለሙያው፤ ይህ ካልሆነ ግን የጡቱ ጫፍ እንዲቆስል ምክንያት ይሆናል ብለውናል፡፡

እናቶች እያጠቡ ሳለ አንዱ ጡት ቢፈስ ጡቴ ፈሰሰ ብለዉ የሚጠባዉን ልጁ ወደሌለኛዉ ጡት የሚቀይሩ ከሆነም ለምግብ እጥረት እንዲጋለጥ ምክንያት ይሆናል ምክኒያቱም ደግሞ የእናቶች የመጀመሪያዉ የጡት ፍሳሽ ዉሃ ስልሆነ ነዉ ይላሉ፡፡

እናቶች ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ ያህል ልጁን አንዱን ጡት ብቻ ማጥባት አለባቸዉ ብለዋል ባለሙያው፡፡
ሌላዉ እናቶች ካጠቡ በኋላ አስገስትዉ ማስተኛት አለባቸዉ፣ ሳያስገሱ ቢተኙ የጠቡት ወተት ትን ብሏቸዉ ወደሳንባቸዉ ዉስጥ በመግባት ሊገላቸዉ ይችላል፡፡

ሌላዉ እናቶች በድህረ ወሊድ ወቅት ሊያዉቁት ከሚገባዉ ነገር የጸሃይ ብረሃን እንዴት ማሞቅ አለባቸዉ የሚለዉን ነዉ ብለዉናል ባለሙያዉ መዝግቡ ጫንያለዉ፡፡

የመጀመሪያዉ እናቶች ብዙ ጊዜ የሰዉ አይን ፍራቻ እንዲሁም ብርድ ልጄን ይመታዋል እያሉ በመስታወት ወደ ቤት ዉስጥ በሚገባ የጸሃይ ብረሃን ልጃቸዉን ያሞቃሉ፤ ያ ደግሞ ልጁ በቀጥታ ማግኘት ያለበትን ያህል የጸሃይ ብረሃን እንዳያገኝ እና ለተለያዩ በቫይታሚን ዲ ( vitamin D) እጥረት ምክንያት በሚመጣ በሽታ እንዲያዝ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ከጥዋቱ 3-5 ሰኣት ያለዉ ጊዜ ጸሃይ ለማሞቅ ተመራጭ ነዉ፣ ድንግት ዝናብ ቢሆን ግን ከሰኣት በኋላ 10 ሰኣት ላይ ማሞቅ ይቻላል ይላሉ፡፡
ሌላዉ እናቶች ልጃቸዉን ጸኃይ በሚያሞቁበት ወቅት ምንም አይነት ቅባት፤ቅቤ፤ቫዝሊን መቀባት የለባቸዉም፣ ነገር ግን አሙቀዉ ቤት ከገቡ በኋላ መቀባት ይችላሉ ብለዉናል፡፡

በተጨማሪም ወንድ ልጅ ከሆነ ጸኃይ በሚያሞቁበት ወቅት ብልቱ አካባቢ ጨርቅ ጣል ማድርግ አለባቸዉ የሚሉት ባለሙያው፤ምክንያቱም ደግሞ የጸኃይ ጨረሩ ፍሬዉን እንዳይጎዳዉ ለማድርግ ሲባል ነዉ፤ እንዲሁም አይናቸዉ ላይም ጨርቅ ጣል ማድርግ መረሳት የለበትም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በክርምት ለሚወለዱ ልጆች እና በቂ የሆነ የጸሃይ ብረሃን በማይኖርበት አከባቢ ደግሞ ከህክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር የቫይታሚን ዲ መድሃኒት እንዲወሰድ ማድርግ አለባቸዉ ሲሉ ሙያዊ ምክር ሰጥተዋል፡፡

#መረጃውን የሰጡን አቶ#መዝገቡ ጫንያለዉ #የካ ክ/ከ የካ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ እና አስተኝቶ ማከም ዲፓርትመንት ሀላፊ ናቸው፡፡

#በልዑል ወልዴ

መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply