በድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት ባለቤት በሆኑት ሲትራ ጀማል የሚመራው የስ የውበት ማሰልጠኛ ተቋም  ለመጀመሪያ ጊዜ ያስልጠናቸውን 20 ተማሪዎችን አስመረቀ ።የሜክፕ ባለሞያና መምህርት ሲትራ ጀማል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/DCKVWVdz84_HrXpXtQ4iCK24MXju64Y7TKOZkpp1ol2trqwxHEDCrtAUfhR8a0nhxTB5gf_nfEqJM7ZLXUWS1uT8A5WIbg0VHgx9qs0EMprEHc0jzVbQ-Ku_jqguBQQJy8DAo8CFHDO1BmwQDvP2E--x2Xu0mddpzZdMxExPenhngXFv6LTIAtCGcydmiluWRp_GgLgxxlG7uroowQ9dkDNVZOYqchKb8foNSr0ZW9tjR1ZEj4ufrRk0Dofxza01NqR2b4SgRuNpi0sTRwNfVjmO3UmU-TUkOHlJa3rMwCrOtqXYWu8ZPVObaSU0LR9xh_aE3qbOTM9AcvayXA8Urw.jpg

በድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት ባለቤት በሆኑት ሲትራ ጀማል የሚመራው የስ የውበት ማሰልጠኛ ተቋም  ለመጀመሪያ ጊዜ ያስልጠናቸውን 20 ተማሪዎችን አስመረቀ ።

የሜክፕ ባለሞያና መምህርት ሲትራ ጀማል እንዳሉት እነዚህ ተማሪዎች በፊልም ኢፌክት፣ በቢዩቲ ሜካፕ፣በጥፍር ስራ፣በፕሮቶኮልና በአይ ላሽ ለአንድ አመት ሲሰለጡኑ  ቆይተዋል።

ባለሙያዋ ተማሪዎቹ  ስልጠናውን  በዘረፉ ላይ ዘለግ ያለ ዓመት የስራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ተደግፈው ቢቂ  የተግባር ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸው ገልፀዋል ።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙት ድምጻዊ ኢሳያስ ታምራት በበኩላቸው በምረቃ ስርዓቱ ላይ የተገኙት “የባለቤታቸውን ሲትራ ጀማል ስኬት ለመቋደስና ስራቸውን ለማበረታታት እንደሆነ ተናግረዋል ።

የስ የውበት ማሰልጠኛ በዋናነት “ሴቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ ዓላማ “ያለው ተብሏል።

ባለቤቶቹ እንዳሉት እኚህ ተማሪዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ገብተው ማህበረሰቡን በልዩ ልዩ መልኩ ለማገልገል በሚችሉበት ዘንድ ብቁ ሆነው ነው የወጡት ብለውናል።

በመጨረሻም ድርጅቱ በቀጣይ በስፋት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በመሰናዳት ላይ ይገኛል ብለዋል ።

በልዑል ወልዴ

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply