You are currently viewing በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ 9 የአማራ ተማሪዎች ታሰሩ፤ 6ቱ ፍ/ቤት ቀርበው ለመጋቢት 7 ሲቀጠሩ፣ የካቲት 29 የታሰሩት 3ቱ ደግሞ አመሻሹን መለቀቃቸው ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የ…

በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ 9 የአማራ ተማሪዎች ታሰሩ፤ 6ቱ ፍ/ቤት ቀርበው ለመጋቢት 7 ሲቀጠሩ፣ የካቲት 29 የታሰሩት 3ቱ ደግሞ አመሻሹን መለቀቃቸው ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የ…

በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ 9 የአማራ ተማሪዎች ታሰሩ፤ 6ቱ ፍ/ቤት ቀርበው ለመጋቢት 7 ሲቀጠሩ፣ የካቲት 29 የታሰሩት 3ቱ ደግሞ አመሻሹን መለቀቃቸው ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎችን ማሰሩ፣ ማሳደዱ እና ማዋከቡ ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ተገልጧል። ዩኒቨርስቲውም ሆነ የተማሪዎች ህብረት በአማራ ተማሪዎች ላይ በተለዬ መንገድ እየደረሰ ያለው በደል እያሳሰባቸው ባለመሆኑ ያለጥፋታቸው ለእስር እየተዳረጉ፣ እየተሳደዱ እና እየተዋከቡ መሆኑን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተናግረዋል። እንደአብነትም የካቲት 26/2015 ማታ ላይ ከቤተ ክርስቲያን ቆይተው ወደ ግቢ እየገቡ በነበሩ ተማሪዎች ላይ መንገድ ላይ ተደብቀው የቆዩ ኦነጋዊ ፍላጎት እና አላማን ያነገቡ ጋኦ (GAO) የሚል የሽፋን አደረጃጀት መስርተዋል ያሏቸው ተማሪዎች ድንጋይ በመወርወር ሁከት ፈጥረዋል። በእለቱ አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች አቀባበል እየተደረገ እንደነበርም ተገልጧል። በወቅቱ መታሰር እና በህግ መጠየቅ ያለባቸው ተደራጅተው ጥቃት እያደረሱ ያሉ አካላት መሆን ሲገባቸው በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአማራዎች ላይ ዘምተዋል ብለዋል። በዚህም ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል እየሸሹ የነበሩ 6 የአማራ ልጆች በሳቢያ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፤ ከእነዚህም መካከልም ብዙዎች በዚህ ዓመት ተመራቂዎች ናቸው ሲሉ አክለዋል። የካቲት 28/2015 ፍ/ቤት ቀርበውም ለመጋቢት 7/2015 ተቀጥረዋል። በግፍ እስር ላይ የሚገኙትም:_ 1) ግዛቸው በቃሉ፣ አይቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪ፣ 2) አሌ ሞላዬ፣ስፖርት ሳይንስ የ4ኛ ዓመት ተማሪ፣ 3) ዳዊት አደራጀው፣ ስፖርት ሳይንስ የ3ተኛ ዓመት ተማሪ፣ 4) መልካሙ ካሳ፣ ሲቪክስ የ3ተኛ ዓመት ተማሪ፣ 5) አስችል ሹመት፣ማትስ የ4ኛ ዓመት ተማሪ፣ 6) በረከት ምናለ፣ አማርኛ 3ተኛ ዓመት ተማሪ ናቸው። በግቢው ውስጥ “ይሄ የእኛ ሀገር ነው፤ ነፍጠኛ ይውጣልን” የሚሉ ጽንፈኛ ኦነጋዊያን አሉ ተብሏል። “ተጨቁነናል” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ግቢው በአብዛኛው በኦሮሞ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት የተያዘ ነው ብለዋል። “የግቢው ፕሬዝዳንት እየመራችን አይደለም፤ ዩኒቨቲውም ሆነ የተማሪዎች ህብረት ችግራችን እየፈታ አይደለም፤ ዋስትና የለንም” ሲሉ ተደምጠዋል። በተመሳሳይ የካቲት 28/2015 በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ ያለበደላቸው በግፍ የታሰሩት ተማሪዎች ይለቀቁ በሚል የርሃብ አድማ ካደረጉ ተማሪዎች መካከልም:_ 1) ክፍሌ አደራው፣ 2) ሀብታሙ አለሙ እና 3) ሀቢብ መሀመድ የተባሉ የሚገኙበት ሲሆን አመሻሹን ሶስቱም ተፈተዋል። ፎቶው በእስር ላይ ካሉት አንዱ _የዳዊት አደራጀው ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply