You are currently viewing በድርቅ እና ረሃብ ምክንያት በኢትዮጵያ የምግብ ቀዉስ ይከሰታል ስትል እንግሊዝ አስጠነቀቀች፡፡

በድርቅ እና ረሃብ ምክንያት በኢትዮጵያ የምግብ ቀዉስ ይከሰታል ስትል እንግሊዝ አስጠነቀቀች፡፡

በትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ የሚገኘዉ አይደር ሆስፒታል የህጻናት ክፍል ያለዉ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ስትል ነዉ የገለጸችዉ፡፡

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተዉ የምግብ ቀዉስ ያስከተለዉ ጉዳት በግልጽ የሚታይባቸዉ ህጻናት በክፍሉ ዉስጥ ተኝተዉ ይታያሉ ነዉ የተባለዉ፡፡

ህጻናቶቹ ከፍተኛ በሆነ የምግብ ዕጦት እየተሰቃዩ መሆናቸዉ በግልጽ የሚታይ ነዉ ተብሏል፡፡

በክፍሉ ዉስጥ በአልጋዎቹ ጫፍ ላይ የተቀመጡት እናቶች ልጆቻቸዉን ቢያንስ ከረሃቡ ያስታግስላቸዉ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ የደረቁ ጡቶቻቸዉን ሲመግቧቸዉ ይታያል ሲል ያክላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

ኢትዮጵያ ረሃብ እና ጦርነት በሚባሉ መንታ ጨካኞች እየተሰቃየች ነዉ የሚለዉ ዘገባዉ፤ በጦርነቱ ምክንያት እርሻዎች እና የምግብ እህሎች በመዉደማቸዉ ምክንያት ብዙዎች ለከፍተኛ ረሃብ እና ድርቅ ተጋልጠዋል ብሏል፡፡

ይሆን እንጂ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ሺፈራው ተ/ማርያም ድርቅን ለፖለቲካዊ ዓላማ መጠቀም “ተገቢ ያልኾነ” እና “ፍጹም ተቀባይነት የሌለው” ድርጊት ነው በማለት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የዓለማቀፍ ተቋማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርቡ ያካሄዱት የዳሰሳ ጥናት፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው ድርቅ እንጂ ርሃብ እንዳልኾነ ማረጋገጡን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል ተብሏል።

ኮሚሽነር ሺፈራው፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊ እንደሆኑ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት፣ በ11 ቢሊዮን ብር ወጪ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል የዕርዳታ እህል ለተረጂዎች ማከፋፈሉን እንደጠቀሱ ዘገባው አመልክቷል

እስከዳር ግርማ
ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply