በድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ሶስት አማራዎች ሲገደሉ ሁለት ቆስለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 12 ቀን 20…

በድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ሶስት አማራዎች ሲገደሉ ሁለት ቆስለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 20…

በድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ሶስት አማራዎች ሲገደሉ ሁለት ቆስለዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሳስማንደን በተባለ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎችና ተባባሪዎች በጥይትና በቀስት በመታገዝ በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። በጥቃቱም ሶስት አማራዎች ሲገደሉ፣ ሁለት መቁሰላቸውን ነው ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ያመለከተው። ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት የደረሰ ሰብላቸውን በመሰብሰብ ላይ በነበሩ 3 አማራዎች ላይ የተደራጁ ነፍሰ ገዳይ የጉምዝ ታጣቂዎች በቀስት በማሳደድ አንዱን ሲገድሉ ሁለቱ አምልጠዋል። በሳስማንደን ቀበሌ ልዩ ስሙ ዲዎን በተባለ ጎጥ ነው በተለያዩ የአካል ክፍሎቹ ላይ በጨካኞች ቀስት ተወግቶ በግፍ የተገደለው ብለዋል ነዋሪዎቹ። ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ ተኩስ በመክፈት ተጨማሪ ሁለት አማራዎችን ገድለዋል፤ ሌሎች ሁለት አማራዎችንም ስለማቁሰላቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። “በመተከል አማራ ላይ የሚፈፀመው የግፍ ግድያ መቼ ነው የሚያቆመው?” ሲሉም እስካሁን መልስ ያላገኘ ጥያቄ አቅርበዋል_ በመተከል የድባጤ ነዋሪዎች። ይህን ተከትሎም የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ወደ ሳስማንደን ቀበሌ አመሻሹን ስለመግባታቸው የተናገሩት ምንጮች ስርዓተ ቀብራቸው በነገው እለት ይፈፀማል ብለዋል። “መተከል ላይ በየጊዜው የሚፈሰው የአማራ ደም እንዲቆም የሚያደርግ አንዳች መፍትሄ ሰጭ አካል እስካሁን አልተገኘም” ሲሉ ነዋሪዎች በየጊዜው እያማረሩ እና የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply