በድባጤ ወረዳ በርበር ቀበሌ አንድ አማራ በጉምዝ ታጣቂዎች በጥይት መገደሉ እና 6ቱ ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ…

በድባጤ ወረዳ በርበር ቀበሌ አንድ አማራ በጉምዝ ታጣቂዎች በጥይት መገደሉ እና 6ቱ ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

በድባጤ ወረዳ በርበር ቀበሌ አንድ አማራ በጉምዝ ታጣቂዎች በጥይት መገደሉ እና 6ቱ ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በርበር ቀበሌ ሼህ ሁሴን ሞላ ከጉምዝ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል። ሼህ ሁሴንን ጨምሮ 7 አማራዎች በማሳቸው ላይ ሳሉ ነው በሽብር ተግባር የተሰማሩ የጉምዝ ታጣቂዎች ለመግደል ያሯሯጧቸው ሲሆን 6ቱ ስለማምለጣቸው ነው ምንጮች የተናገሩት። በጋሌሳ ቀበሌ ቱስኪ ጎጥ አካባቢ 17 የሚሆኑ የአማራ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈው ወስደዋል ተብሏል። በትናንትናው እለት መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ሌሎች የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው ማቅናታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በአርሶ አደር ሁሴን ላይ ከተፈፀመው ግድያ እና ሌሎችን ከማሳደድ ጋር ተያይዞም ለደህንነታቸው የሰጉ በርካታ የበርበር ቀበሌ አማራዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply